በሻሸመኔና ዝዋይ የተቀሰቀሰው ጸረ ወያኔ ተቃውሞ ተቀጣጥሏል ወደ መሃል ሃገር የሚወስዱ መንገዶች ተዘግተዋል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በሻሸመኔና ዝዋይ የተቀሰቀሰው ጸረ ወያኔ ተቃውሞ ተቀጣጥሏል ወደ መሃል ሃገር የሚወስዱ መንገዶች ተዘግተዋል::
#Ethiopia #Oromoprotests #Shashemene #Ziway #EPRDF #Miniliksalsawi

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የወያኔ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ የተያያዘውን ትግል ስም ለማጥቆር ሲል በብሄሮች መካከል የሃይማኖት ግጭት ያለ ኣስመስሎ ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ነው።በደቡብ ኢትዮጵያ ሻሸመኔ የተነሳው ጸረ ሕወሓት ተቃውሞ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ከባሌ ተነስቶ ወደ መሃል ሃገር የሚያስገቡ መንገዶች ከመዘጋታቸው የተነሳ የአከባቢው የትራንስፖርት እና የመንግስት ስራዎች ግንኙነት ቆሟል:: እንዲሁም በዝዋይ ባቱ የተነሳው ተቃውሞ ተከትሎ የአግኣዚ ሰራዊት ወታደሮች ተማሪዎችን ሲያሳድዱ የተስተዋለ ሲሆን በከተማዋ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን በአከባቢው የተሰማሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች ሪፖርት አድርገዋል::በምስራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ወረዳ የተነሳው ተቃውሞ የ60 አመት አዛውንት የሆኑት ወይዘሮ ጁሃራ ሙሳ የተገደሉ ሲሆን እንዲሁም ሌላ አዛውንት ሴት ቆስለው በጋራሙለታ ሆስፒታል እየታከሙ ይገኛሉ::በተጨማሪ መረጃ በዚሁ ወረዳ አደም አብደላ የተባለ ገበሬ መገደሉ ታውቋል::
በምጥራብ አርሲ ኮፈሌ አከባቢ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ መሆኑን በአከባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች የላኩት መረጃ ሲጠቁም የአግኣዚ ጦር ከዚህ ቀደም ሙስሊም ወንድሞቻችንን እንደጨፈጨፈው አሁንም የኮፈሌን ሕዝብ በተኩስ እያሸበረው እንደሚገኝ መረጃዎቹ ጠቁመዋል::በጠዋት በ6 ወታደራዊ ካሚዮን ተጭኖ ወደ ኮፈሌ የዘለቀው የአግኣዚ ጦር አከባቢውን እያሸበረው እንደሚገኝ ታውቋል::

በምስራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ወረዳ የተነሳው ተቃውሞ የ60 አመት አዛውንት የሆኑት ወይዘሮ ጁሃራ ሙሳ የተገደሉ ሲሆን እንዲሁም ሌላ አዛውንት ሴት ቆስለው በጋራሙለታ ሆስፒታል እየታከሙ ይገኛሉ::በተጨማሪ መረጃ በዚሁ ወረዳ አደም አብደላ የተባለ ገበሬ መገደሉ ታውቋል:: #MinilikSalsawi
ይህ በእንዲህ እንዳለ የወያኔ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ የተያያዘውን ትግል ስም ለማጥቆር ሲል በብሄሮች መካከል የሃይማኖት ግጭት ያለ ኣስመስሎ ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ነው። ህዝባችን ይህንን ተገንዝቦ የስርኣቱ ቅጥረኞች በህዝብ ተመስለው የጥፋት ተልእኮኣቸውን እንዳይፈፅሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል። በዚህም መልኩ፣
1.ሁሉም የሃይማኖት ተቁዋማት ጥብቅ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል። ይህንን ለማሳካት የተለያዩ ሃይማኖት ተከተይ የሆናችሁ ታጋዮቻችን መረጃን በንቃት በመቀባበል በመስጊዶችና በኣብያተ-ክርስቲያኖች እንዲሁም በመቃብር ስፍራዎች ላይ ምንም ኣይነት ጥቃት በጥፋት መልእክተኞቹ እንዳይደርስ መጠበቅ።
2.ኦሮምያ ውስጥም ሆነ በኣጎራባች ኣካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ማናቸውም ብሄር ብሄረሰቦች መነካት የለባቸውም። በሚስተጋቡት መፈክሮች መካከል ምንም ኣይነት ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችን ማስቀየም የሚችሉ ቃላቶች መጠቀም ተገቢ ኣይደለም። ሰላማዊ ሰልፍ በሚካሄድበት ወቅት በተቻለ መጠን የሌሎች ብሄር ብሄረሰብ ተወላጆች በሚበዙባቸው ቀበሌዎች ውስጥ ባይሆን ይመረጣል። ይህም የስርኣቱ የጥፋት መልኣክተኞች ግጭት ለመጫር የሚረዳቸውን ኣጋጣሚ ይቀንሰዋል።
3.የግል ንብረቶች ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባቸዋል እንጂ የጥቃት ኢላማ መሆን የለባቸውም። የኦሮሞም ሆነ የማንኛውም ብሄር ተወላጅ የግል ንብረት መነካት ኣይኖርበትም። ሾልከው እየገቡ ወጣቶቻችንን ለማሳሳት የሚፈልጉ ጠብ-ኣጫሪ የጠላት ተላላኪዎችን ኣንቅስቃሴ በንቃት መከታተልና የጥፋት ኣላማቸውን ማክሸፍ ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት።
4.ማህበራዊ ኣገልግሎት ሰጪ የሆኑት የመንግስት ተቁዋማት እንዳይነኩ መጠንቀቅ ያሻል። ከነዚህም መካከል የጤና ተቁዋማት፣ ኣምቡላንሶች፣ ትምህርት ቤቶች ወዘተ ዛሬም ሆነ ነገ ህዝብን ስለሚያገለግሉ በንቃት ሊጠበቁ ይገባል።