የሃይሉ ሻውል መኢአድ ፓርቲ እርስ በርሱ ሲባላ በደቡብ የወያኔ-ደህንነት ቢሮ ሶስት የተቃዋሚ አመራሮችን አፍኗል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የሃይሉ ሻውል መኢአድ ፓርቲ እርስ በርሱ ሲባላ በደቡብ የወያኔ-ደህንነት ቢሮ ሶስት የተቃዋሚ አመራሮችን አፍኗል:: #Ethiopia #EPRDF #AEUO #SLM #MinilikSalsawi
ወያኔ ሰላማዊ ፓርቲዎችን እና አመራሮችን ማሸበሩን ቀጥሏል::በኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ፓርቲ መኢአድ ውስጥ በፕሬዚደንቱ አበባው መሃሪ እና በማእከላዊ ምክር ቤቱ መካከል በተነሳው አምባጓሮ ደክሞ የነበረው ፓርቲ ተሽመድምዶ እየሞተ ነው ሲሉ አባላቱ ማማረራቸው ሲታወቅ አቶ አበባ ያልታወቀ ሃይል መከታ በማድረግ የፍርድ ቤት ማገጃ በመጣስ ማህተሙን ለሕገወጥ ስራ እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ አባላቱ ይናገራሉ::
አቶ አበባው መሃሪ በመኢአድ ማዕከላዊ ምክርቤት በጥር 15 ቀን, 2008 ዓ.ም ከፕሬዚዳንትነት ሃላፊነታቸው የማንሳቱን ውሳኔ እና በጥር 23 ቀን, 2008 ዓ.ም በፍርድቤት ተከሰው የድርጅቱን ማህተም እንዳይጠቀሙ መታገዳቸውን አምነው እና አክብረው ከተቀበሉ በኋላ ፤በህገወጥ መንገድ የፓርቲው ማዕከላዊ ምክር ቤትን ውሳኔ እና የፍርድቤት የዕግድ ትዕዛዝ በመጣስ የፓርቲውን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ እንድሪያስ ጨምሮ ሌሎች የላዕላይ ምክር ቤት አባላትን በግላቸው አግጃለው እያሉ ደብዳቤ እያሰራጩ መሆኑ ስለተደረሰባቸው ፓርቲው በማጭበርበር ወንጀል ሕግ ሊጠይቃቸው ነው ። ሲሉ አባላቱ ተናግረዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ክልል ሲዳማ አርነት ንቅናቄ አመራሮች ባለታወቀ ምክንያት ከያሉበት በደህንነት ሃይሎች ታፍነው መታሰራቸው ታውቋል።በዚህም መሰረት የታፈኑ አመራሮች
1ኛ ደሳለኝ ሜሳ(ሲአን ፖሊቲካ ዘርፍ ኃላፊ )
2ኛ ተሾመ ደበበ (የሲአን ወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ)
3ኛ ደበሳ ዳካ ( የሲአን ቱላ ዞን ሊቀመንበር) ሲሆኑ የደቡብ ክልል ደህነቶችና ፖሊሶች ተባብረው አመራሮቹ በማፈን ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች መወሰዳቸው ታውቋል::
