ከሁለት ወር በፊት የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ የደህንነት ቢሮው አለመተማመን ሰፍቷል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከሁለት ወር በፊት የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ የደህንነት ቢሮው አለመተማመን ሰፍቷል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthiopianSecurity‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎ChangeinEthiopia‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) : የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋ ለሹሞቻቸው እና አባሎቻቸው የዛቱበትና የወልደስላሴ እጣ ካማራቹ በያዛቹን መስመር ቀጥሉ ብለው ያስፈራሩበት ግምገማ እና አባላቱን ከሞባይላቸው ጀምሮ እስከ ቤት ጓዳቸው የተፈተሸበት ግምገማ ካለቀ በኋላ በደህንነት ቢሮ ውስጥ አለመተማመኑ ከመስፋቱም በላይ የደህንነት ከፍተኛ ሹሞች በሁለት መንገድ ከቢሮው ይወገዳሉ ተብሎ ይጠበቃል::በከፍተኛ ደረጃ መሰሪ እና አድብቶ አጥቂ እንዲሁም በቅርቡ የሲአይኤ ተባባሪ አባል ሆነው የታጩት በመለስ ዜናዊ አስተዳደር ወደ ጎን ተገፍተው መለስ ከሞተ በኋላ የአንበሳውን ድርሻ የያዙት አቶ ጌታቸው አሰፋ ወይዘሮ አዜብን ጨምሮ ከምክትላቸው ከአቶ ወልድስላሴ ጀምሮ የሚፈታተኗቸውን ባለስልጣናት እና ባለሃብቶች እርምጃ ወስደውባቸዋል ሲሉ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::

በደህንነት ቢሮ ውስጥ እንደ መርዝ ጦር የሚፈሩት አቶ ጌታቸው ገነው ለመውጣት የማይፈልጉ ሲሆኑ በደህንነት ባለስልጣናት እና በአባላቱ መካከል አለመተማመ እንዲኖር እርስ በእርስ እንዲፈራሩ እና በግምገማ አንዱ ሌላውን እንዲያንኳሥ እንዲሁም የሌሎች ብሄር አባላት አንገታቸውን እንዲደፉና በሽብር በጥርጣሬ እና በፍርሃት እንዲኖሩ የሚሰራ ቡድን እንዳላቸው ይታወቃል::ባለፍው የተካሄደው ግምገማ የፈጠረው አልመተማመን 132 የደህንነት አባላት ስራቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ ማመልከቻ ያቀረቡ ሲሆን ውጭ አገር ለትምህርት ተልከው የነበሩ የኦሮሞ ብሄር የደህንነት አባላትም በድንገት ወደ አገር ቤት በማስመጣት ትምህርታቸውን እንዳይቀጥሉ መደረጉ ምንጮች ተናግረዋል::

ከሁለት ወር በፊት የተካሄደው ግምገማ በተለይ የሕወሓት ሰዎች የሆኑትን የትግራይ ተወላጆች ያላጠቃ እና የሌሎች አባላት መብት የገፈፈ ያዋረደ መሆኑ በቢሮው እስጥ ያለውን የአለመተማመን መንፈስ ያሰፋ ሲሆን አባላቱ አንገታቸውን እንዲደፉ ከማድረጉም በላይ እርስ በእርስ እንዲናቆሩ በፊትም የራስ መተማመን የሌላቸው ከመሆኑም በላይ ከቀድሞ በበለጠ ራሳቸውንም እንዳያምኑ አድርጎ የሰበራቸው መሆኑ ሲገለጽ ምንጮቹ እንዳሉት በደህንነት ቢሮ ውስጥ የበላይነት ለመያዝ ተቃርቦ የነበረው የብአዴን አባላት ሃይል አከርካሪው የተመታበት ግምገማ የነበር መሆኑን ገልጸዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬