በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ደዋጨፋ ወረዳ በደረሰ ከባድ የመኪና አደጋ የ9 ሰው ሕይወት አለፈ:: (VIDEO)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Oromia Zonecomunication Kamise's photo.

በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ደዋጨፋ ወረዳ ቦርከና ፍልውሃ አካባቢ ሂጅራ በተባለ ቦታ በደረሰ አደጋ 2 የህዝብ ማመላለሻዎች ተጋጭተው በደረሰ ከባድ የመኪና አደጋ ለጊዘው የ9 ሰው ሕይወት ሲያልፍ ቁጥሩ ያልታወቀ ተሳፋሪ ከባድ እና ቀላል አካልጉዳት እንደደረሰበት ተገለጸ፡፡

ዛሬ በግምት ከጠዋቱ ሶስት ሰአት አካባቢ በ3/6 2008 ዓም ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ያለው ኮድ 3 አዲስ አበባ ታርጋው 69893 የሆነ ታታ ደረጃ አንድ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከማጄቴ ወደ ከሚሴ በመጋዝ ላይ ያለው አይሱዙ ኮድ 3 አማራ ታርጋው 07929 የሆነ ቅጥቅጥ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ቦርከና ፍልውሃ አካባባቢ ሂጅራ በተባለ ቦታ ሙሉ ተሳፋ ሪ እንደጫኑ ተጋጭተው ከፍተኛ የሂወት እና የንብረት ጉዳት ደርሷል ሲሉ የደዋጨፋ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ኢንስፕክተር ሰይድ ጦላሃ አስረድተዋል ፡፡

Oromia Zonecomunication Kamise's photo.

በዚሁ እለት በደረሰው አደጋ እስካሁን የቅጥቅጡን የአይሱዙ ሾፌር ጨምሮ 9 ሰዎች ሂወት ማለፉ ሲረጋገት ከባድ እና ቀላል ቁስለኞች ወደ ከሚሴ እና ደሴ ሆስፒታል በመጓጓዝ ላይ ሲሆኑ ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ከፖሊስ አካላት በተሰጠው አስተያየት የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ሀይወታቸው ያለፉ የ7 ሰዎች አድረሻ ተለይቶ ወደ የቤተሰባቸው የተላከ ሲሆን አሁንም አድራሻቸው ያልተለየ 2 ሰዎች አስክሬን በከሚሴ ሆስፒታል ተቀምጦ አድረሻቸውን ፖሊስ የማፈላለግ ስራ እየሰራ ነው፡፡
[youtube http://www.youtube.com/watch?v=Um8y5Unu25o]

Oromia Zonecomunication Kamise's photo.
Oromia Zonecomunication Kamise's photo.
Oromia Zonecomunication Kamise's photo.