ጄኔራሉና ባለቤቱ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጄኔራል በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ይባላሉ። የህወሃት አንጋፋ ታጋይ ሲሆኑ በአብዛኛው አባል የሚጠሩት “በርሄ ሻእቢያ” በሚል ነው። ስመ ጥር የጦር አዋጊ ናቸው። በባድመ የተካሄደውን ውጊያ ከመሩትና ሻዕቢያን ከደቆሱት የጦር አዛዦች አንዱ ነበሩ። ብ/ጄ/ል በርሄ የሚታወቁበት ሌላው ባህርይ ለእውነት የቆሙ፣ ያመኑበትን የሚፈፅሙና ሌብነትን የሚጠየፉ መሆናቸውን የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ። በ1993 ዓ.ም ጦርነቱ እንዲቆም ያዳረጉት መለስ ዜናዊ ላይ ክፉኛ ተበሳጭተዋል። በዛው ወቅት መለስ ቤተመንግስት ጄኔራሎችን በመጥራት ህገ መንግስቱን የጣሰ ስብሰባ ማካሄድ ይዘዋል። ጄ/ል ታደሰ (ጋውና) መለስንና ስብሰባውን በመቃወም ጥለው ወጡ። ሌሎች የጦር አዛዦች በህገ ወጥ እንዲባረሩ ማድረግ ቀጥለዋል። ጄ/ል በርሄ ከአዲግራት በሂሊኮፕተር እየከነፉ ሲጓዙ አስቀድመው በስፍራው ለነበሩ ጓዶቻቸው መለስን ለማስወገድ እየሄዱ መሆኑን ተናግረዋል። በርሄ አድርጋለሁ ያሉትን እንደሚፈፅሙ ሁሉም ያውቃሉ። አመሻሽ ላይ ደብረ ዘይት ደረሱ። ከዚያም ቤላ ወደሚገኘው የጦር ካምፕ አመሩ። በማግስቱ ወደ ቤተመንግስት አምርተው ያቀዱትን ሊፈፅሙ ነው። በካምፑ ከበረሀ አንስቶ የሚያውቋት ታጋይ ባለቤታቸው (ሻምበል) እና ሁለት ልጆቻቸው ጋር ደርሰው ምሽቱን አሳለፉ። ጠዋት ግን የታየው የሚዘገንን ነገር ነበር። የጄ/ል በርሄ ሰውነት በበርካታ ጥይት ተበሳስቷል። ከአልጋው አጠገብ ጋደም ያለችው ባለቤታቸው ጭንቅላቷ በጥይት ተበርቅሶ በአሰቃቂ ሁኔታ ሞታለች። እንደአጋጣሚ በሌላ ክፍል የተኙት ልጆች የተፈጠረውን ዘግይተው ነበር የሰሙት። በማግስቱ ኢቲቪ ያስተላለፈው ዜናና በትግርኛ የተሳራጨው የተለያዩ ነበር። በአማርኛ “ጄ/ል በርሄ በሻምበል ባለቤታቸው ተገደሉ። እሷም ራሷን አጠፋች” ሲል በትግርኛ ደግሞ “በትዳራቸው ላይ በተፈጠረ ያለመግባባት ተገዳደሉ” የሚሉ ነበሩ። በካድሬዎቹ ለጦሩ አባላትና መኮንኖች የተነገረው እጅግ አሳፋሪ ነበር። ይህን ግድያ የፈፀመው ዛሬ እስር ቤት የሚገኘው የቀድሞ የደህንነት ሹም ወ/ስላሴና ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ እንደሆኑ ማስገንዘብ ያሻል።