የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አባል የሆነችው ወ/ሪት መስከረም ያረጋል፣ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባት እንደሚገኝ ገለፀች፡፡
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በመስከረም ያረጋል ላይ ዛቻና ማስፈራሪያው ቀጥሏል
የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አባል የሆነችው ወ/ሪት መስከረም ያረጋል፣ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባት እንደሚገኝ ገለፀች፡፡
ጥር 28 ቀን 2008 ዓ.ም ከፒያሳ አስኮ ወደሚገኘው ቤቷ በማምራት ላይ ሳለች ሁለት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ተከታትለዋት ወደ ታክሲ እንደገቡ ያስተዋለችው መስከረም፣ ከታክሲው ወርዳ አራዳ አካባቢ ወደሚገኝ ካፌ ብታመራም፤ ካፌው ድረስ ተከታትለዋት የገቡት ሰዎች የተጠቀመችውን ውሃ ከፍለው ‹‹ቀንሽን ጠብቂ!›› የሚል ዛቻ አድርሰው ከቦታው ተሰውረዋል፡፡ ከእነዚህ ግለሰቦች መካከል አንደኛው ግለሰብ ትላንት የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ.ም ከአስኮ ወደ ፒያሳ በማምራት ላይ ሳለች ተከታትሏት ታክሲ ውስጥ ከገባ በኋላ ከታክሲው ስትወርድ ጠብቆ ‹‹በቅርቡ አባትሽ የገባበት ጉድጓድ እንከትሻለን!›› የሚል ዛቻ አድርሶ ከቦታው መሰወሩን መስከረም ገልፃለች፡፡ ወ/ሪት መስከረም ያረጋል፣ ክስተቱ እንግዳ እንደሆነባትና ይህንን ዛቻና ማስፈራሪያ እያደረሱ የሚገኙ ግለሰቦችን ማንነት ለማወቅ እንደተቸገረች አስረድታለች፡፡
መስከረም ያረጋል፣ ከዚህ ቀደም ከዛቻ ባለፈም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ጥቃት እንደደረሰባት ይታወሳል፡፡
