በወርቅ ፍለጋ የተሰማሩ 85 ወጣት ኢትዮጵያውያን በታጣቂዎች ታፍነው ወደ ኤርትራ ተወሰዱ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በወርቅ ፍለጋ የተሰማሩ 85 ወጣት ኢትዮጵያውያን በታጣቂዎች ታፍነው ወደ ኤርትራ ተወሰዱ። Amdom Gebreslasie

በባህላዊ መንገድ ወርቅ በመፈለግ ስራ ተሰማርተው የነበሩ ወጣቶች የሚበዙባቸው 85 የትዮጵያውያን
ከኤርትራ ድንበር ተሻግረው በመጡ ታጣቂዎች ታፍነው ወደ ኤርትራ መወሰዳቸው ያከባቢው ኑዋሪዎች ገልፀዋል።

ዓፈናው ያጋጠመው በትግራይ በምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሑመራ ወረዳ፣ እድሪስ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዳ’ግርማይ ከተባለ የተከዘ ወንዝ ዳር በ29 / 05 / 2008 ዓ/ም ከጥዋቱ 03:00ና በተመሳሳይ ወረዳ ኣደባይ ቀበሌ ኣዳይቕበፅኒ ከተባለ ቦታ በ29 / 05 /2008 ዓ/ም ከቀኑ 07:00 ሰዓት 85 ወጣቶች ወርቅ በመቆፈር እያሉ ከኤርትራ በመጡ ታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸው ተገልፀዋል።

እንደ ምንጮቻችን ገለፃ ከሆነ በዳ’ግርማይ ኣከባቢ ዓፈና የፈፀሙ ታጣቂዎች ኣንድ ወጣት ተኩሰው ሲገድሉ ሌላ ወጣት ደግሞ ወደ ተከዘ ወንዝ ገብቶ መሞቱን ነው።

ከታጣቂዎች ዓፈና ኣምልጠው ወደ ኣደባይና እድሪስ ከተሞች የገቡ በርካታ ወጣቶች እንዳሉ እየተገለፀ ነው።

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ተከዘ ወንዝ ዳር በባህላዊ መንገድ ወርቅ በማውጣት ተግባር የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የኢትዮ_ኤርትራ ድንበር እየተሻገሩ በሚገቡ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ግዜ ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን ከ2004 ዓ/ም ወዲህ ከ500 በላይ ወጣቶች ታፍነው ኤርትራ መግባታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግስት እነዚህ የኢትዮ_ኤርትራ ድንበር ተሻግረው በመምጣት ዜጎቻችንን በፈለጉት ግዜና ሰዓት እንዳሻቸው ዓፍነው የሚወስዱ ታጣቂዎች ሊያስቆማቸውና የዜጎቻችን ደህንነት በሚገባ ሊያስጠብቅ ይገባዋል።

መንግስት በ85 ዜጎቻችን የተፈፀመው ዓፈና ዙርያ ኣስፈላጊ ማብራርያ ሊሰጥም ይገባዋል እንላለን።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።