የምርጫ ቦርድ ሴራ በዓረና ላይ – ወደ ህገወጥ መንገድ ለማስገባት እየገፋ ነው፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የምርጫ ቦርድ ሴራ በዓረና ላይ
====================================

ዓረና ትግራይ በ2005 ዓ/ም ምርጫ ቦርድ በተገኘበት ጉባኤ አካሂዶ ለምርጫ ቦርድ ሰነዶችን ቢያቀርብም እስካሁን ሰነዶቹ እውቅና እንዳላገኙ በተዳጋጋሚ ደብዳቤዎች እየላከ በተደጋጋሚ ዓረናም በደብዳቤ መልስ ቢሰጠውም ከግዜ ወደ ግዜ ጥያቄዎቹ እየቀያየረ ፍላጎቱ ማብራርያ ሳይሆን ከጉባኤ ውጭ ሕገ ደንባችን እንድንቀይር በማድረግ ወደ ህገወጥ መንገድ ለማስገባት እየገፋን ነው፡፡ባጭሩ እንደሚከተለው አቅርቤላችዋሎሁ

1. ከ 2005 ዓ/ም ጉባኤ በኋላ ከዓረና የተፃፉ ሰነዶች በትግርኛ ማለት በክልሉ የስራ ቋንቋ ነበሩና ወደ አማርኛ እንድንቀይራቸው ትእዛዝ በምርጫ ቦርድ ስለተሰጠን ድሮውንም የአማርኛ ጥላቻ ሳይሆን የክልል ፓርቲ ነን በክልሉ የስራ ቋንቋ እንጠቀም ከሚል አወንታዊ እሳቤ ስለነበረ ሳይከፋን ቀየርን፡፡

2. ሁለት ነጥቦች የያዘ ማብራርያ እንፈልጋለን ብለውን ለሁለቱ ነጥቦች በደብዳቤ ማብራርያ ሰጠናቸው

3. በመቀጠል ሌላ ባለ ስድስት ነጥቦች አዳዲስ ጥያቄዎች የያዘ ማብራርያና ለውጥ እንፈልጋለን ብለው ጠየቁን ለሱም ቢሆን ማብራርያ ለሚያስፈልገው ተሰጥቶ ለውጥ ለሚያስፈልገው ግን የጉባኤ ስልጣን ነው አመራሩ ሕገደንብ የማሻሻል ስልጣን የለውም የሚል መልስ ተሰጣቸው፡፡

4. አሁን ለአራተኛ ግዜ ባለ አስራ አራት ነጥቦችን አዳዲስ ጥያቄዎችንና አንቀፆች የያዘ ለውጥ የሚፈልጉ ጥያቄዎችን ጠይቆናል፡፡ከ አንድ ሕገደንብ በየግዜው እያደገ የሚሄድ ጥያቄ የነገር ፍለጋ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ሊበሏት የፈለጉ አሞራ ጅግራ ይሏታል ይመስላል ነገሩ፡፡

ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች ሕገደንብ ማብራርያ የሚጠይቃቸው በሕገደንባቸው መስራታቸው ለመከታተል እንዲያመቸው መሆኑ እሙን ነው ፡፡እውነት ግን ምርጫ ቦርድ በሕግና ሕገ መንግስት አምኖ ውሳኔ ይሰጣል፡፡እኔ በሕግና ሕገ መንግስት አምኖ ውሳኔ ይሰጣል የሚል እምነት የለኝም ለምን ብትሉኝ ህ.ወ.ሓ.ት በ 1993 ዓ/ም በግልፅ ከ 30 ማ/ኮሚቴ 16ቱ በመገኘት ኮረም ሳይሞላ በ12ቱ የእግድ ውሳኔ ሲያስተላልፍና ያኔ የህ.ወ.ሓ.ት ሊቀ መንበር የነበሩ የከሲሶው በላይ ማ/ኮሚቴ አስቸኳይ ጉባኤ የሚጠይቅ ፊርማ አሻፈረኝ ብለው ሲጥሱ ምን አላቹ፡፡እናንተ የህወሓት ምን እንታዘዝ ባዮች ባትሆኑ ኑሮ ህ.ወ.ሓ.ት ያኔ ስለ ፈረሰ የሁለተኛው ቅንጅትን የሚያክል እውቅናና የሕግ ሸፋን ለማግኘት እንደ አዲስ ፒቲሽን አሰባስቦ መቋቋም ነበረበት ግን አልሆነም በኡነተኛው ህግ ፈርሶ በሃይል ግን አለ፡፡ ስለዚህ እንደ ቅንጅት ያሁኑ ህወሓት የድሮውን ህ.ወ.ሓ.ት ሞክሼ ለመሆን እንኳን የሚያስችለው የሕግ ሸፋን የለውም፡፡

አንድ የገረመኝ ነገር የዋና ፅ/ቤት አድራሻ ህገደንባችን ውስጥ መቐለ ብንልም አድራሻው ተለይቶ መገለፅ አለበት ማለታቸው ነው፡፡ ቤቷ ለይተን በሕገ ደንባችን ብንፅፍ ቤት ኪራይ ለመቀየር ጠቅላላ ጉባኤጠርተንን ሕገደንባችን እንድናሻሽል ከዛ ኪራይ እንድንቀይር መሆኑ ነው ይህ ደግሞ ኪሳራው ግልፅ ነው ፡፡ ዓረና እንደ ህወሓት ቋሚ የሆነ ከህዝብ ቀምቶ የያዘው ፅ/ቤት የለውም፡፡ያሁኑ ህወሓት በድሮው ህ.ወ.ሓ.ት ግዜ የትግራይ ህዝብ በግና ፍየል እያዋጣ የተሰራውን ሓወልቲ ሰማእታት ፅ/ቤቱ በማድረግ ሲጠቀም ዓረና ሲቋቋም ግናት በአርማው የዓዲ ሓቂ ሃወልቲ ሰማእታት ምስል በማስገባታችን የህወሓት ንብረት ነው ብሎ አስቀይሮናል ህወሓት ግና የአክሱም ሃውልት እንደፈለገ አርጎ ይጠቀምበታል፡፡በድሮው ህ.ወ.ሓ. ሊቀመንበሮች በሂወት እያሉ ማውረድም ብርቅ ባልነበረበት እኔ ስልጣን ይብቃኝ ሌላ ይምራ ማለት በተጀመረበት ካንተ የሚበልጥ መሪ ለማጥፋት ሳይሆን ለማፍራትለአንድ በሚደርግበት ገና የግለ ሰው አምልኮ ባልነበረበት ዲሞክራሲያዊት አገር ተስፋ በማድረግ ፈንጅ የማምከን አቅም ባጡበት ግዜ የትግራይ ገበሬ ልጆች ተመድበው ሂወታቸው መስዋእት በማድረግ ለአንድ ፈንጅ አንድ ሂወት ከፍለው በሚያፀዱበት ዘመን በግና ፍየል መሰጠት ኢምንት በነበረበት ህዝብ የሰራውን ባሁኑ ህወሓት ንብረትነት እውቅና መስጠት ክህደት ነው፡፡

ስለዚህ አሁን ለዓረና ም/ቦርድ ከቋንቋ ለውጥ ጀምራቹ ቀጥሎ ባለ ሁለት ነጥብ ጥያቄ ቀጥሎ ባለ ስድስት ነጥብ ጥያቄ አሁን ደግሞ ባለ አስራ አራት ነጥብ ጥያቄ ማብራርያና ለውጥ መፈለጋቹ ያሳዝናል በተለይ የፅፈት ቤቱ ም/ዋና ሓላፊ የአገልግሎቶችና ግንኙነት ዘርፍ ሓላፊ ካሁን በፊትም በትግራይ የም/ቦርድ ፅ/ቤት ሓላፊ ለነበርከው አቶ ወንድሙ ጎሳ ከትግራይ ጀምረህ እስካሁን ለዓረና ያለህ መስተንግዶ እጅግ በጣም ያሳዝናል፡፡

ዓረና ሕገደንቡ ከጉባኤ ውጭ እንዲቀይር በምርጫ ቦርድ ቢገፋም ከጉባኤ ውጭ ሕገደንቡ እንደማይቀይር አስረግጠን በማስገንዘብ አሁን ያለውን ዓረና ችግር ውስጥ አስገብቶ የማፍረስ ሴራ ከህዝባችን በመሆን እንደምንወጣው እንተማመናለን፡፡

ነፃነታችን በእጃችን ነው!!!!!