የጋምቤላ ልዩ ኃይል ትጥቅ ፈታ – VOA


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Gambella, western Ethiopia zones
ከአንድ ሺህ አራት መቶ በላይ ናቸው የሚባሉት የልዩ ኃይሉ አባላት በክልልሉ ዋና ዋና በሚባሉት አኝዋክና ኝዌር ጎሣቸው ተከፋፍለው መጋጨታቸው የተገለፀ ሲሆን ፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ገብተው ሁኔታውን መቆጣጠራቸውን እነዚሁ የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል፡፡

በልዩ አባላት መካከል በተነሣው ግጭት የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ ለጊዜው ዝርዝር መረጃ ባይኖረንም በግጭቶቹ መካከል ግን ሰሞኑን የአንዲት ጎልማሣ ሴት እና የአንድ አምስት ዓመት ሕፃን ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል፡፡ እስከአሁንም ከዘጠኝ መቶ በላይ የሚሆኑ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ካምፕ መግባታቸውና ቀሪዎቹም አየተፈለጉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ጋምቤላ ክልል ውስጥ ከሰማንያ ሺህ በላይ ስደተኞች በተጠለሉበት ፑኝዶ የስደተኞች ሠፈር ውስጥ በስደተኞች መካከል የተፈጠረ ጎራ የለየ ግጭት እንደነበር ተገልጿል፡፡

ስደተኞቹ በአኝዋክና በኝዌር ጎሣዎች ሠፈሮች የተከፋፈሉ እንደሆኑና ባለፈው ሣምንት ውስጥ ደርሷል ከተባለው ብጥብጥ በኋላ ብዙ ስደተኞች ሠፈሮቻቸውን እየጣሉ ከነዋሪው ጋር ተቀላቅለው እንደነበረ በአካባቢው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀውልናል፡፡

በኢታንግ እና በፑኝዶ ሕዝባዊ የሰላም ስብሰባዎች እየተደረጉ ሲሆን ሁኔታው አሁን ወደ መረጋጋት እየተመለሰና ስደተኞቹም ወደ ሠፈሮቻቸው እየገቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ስለስደተኞቹ ሁኔታ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር የኢትዮጵያ ቢሮ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረግን እንገኛለን፡፡

አትዮጵያ ጋምቤላ ውስጥ ባሉ የስደተኞች ሠፈሮች ከ250 ሺህ በላይ ስደተኞችን አስጠልላ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ ዝርዝሩን ያድምጡ። listen