በኦሮሚያ ክፍለሃገር ጉጂ ዞን ተቃውሞ ቀጥሏል::ሰላም ባስ ወደ ኢትዮ ባስ እየተንደረደረ ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኦሮሚያ ክፍለሃገር ጉጂ ዞን ተቃውሞ ቀጥሏል::ሰላም ባስ ወደ ኢትዮ ባስ እየተንደረደረ ነው::
#Ethiopia #Oromoprotests #MIDROC #Guji #SelamBus #MinilikSalsawi #EPRDF
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክፍለሃገር ጉጂ ዞን ሃርቆሌ ከተማ በኦሮሞ ልጆች ላይ የሚደረገው ግድያ እና የሚድሮክ የወርቅ ቁፋሮን በመቃውም ተቃውሞ መቀጠሉ ታውቋል::ከአከባቢው የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ነዋሪዎቹ ከሕጻን እስከ አዛውንት ከከተማው እስከ ገጠር የሚገኘው ሕዝብ በመሰባሰብ ብርቱ ተቃውሞ ማሰማቱ ታውቋል::የክልሉ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር በቢሯቸው የሌሉ ሲሆን የቢሯቸው መታሸግ የተመለከቱ ባቀረቡት ጥያቄ ሙክታር ለሕክምና ባንኮክ መሔዱ ተነግሯቸዋል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመቀሌ ከተማ ተመዝግቦ በመላው ኢትዮጵያ ካለግብር የሚሰራው የወያኔ ንብረት የሆነው የሰላም ባስ የኦሮሞ ሕዝብን ተቃውሞ ተከትሎ በደረሰበት ፍርሃት በስራ ላይ የሚገኙ ያገለገሉ አውቶብሶቹን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ እና ለሶስተኛ ወገን ለማስተላለፍ ማስታወቂያ ማውጣቱ ታውቋል::መስሪ የሆነው የወያኔው አገዛዝ ለዚሁ አላማ ስኬት የሚረዳውን ኢትዮ ባስን በገለልተኛ ስም በአዘጋጅቶ በተዘዋዋሪ ሰላም ባስን ሊያስተላልፍ ወደ ኢትዮ ባስ እየተንደረደረ መሆኑ ለማጣራት በተደረገ ሙከራ የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ
