አዲሱ የወያኔ ካርታና «የህዳሴው» ግድብ ግንባታ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ እንዲሆን የተፈለገበት ሚስጥር (Achamyeleh Tamiru)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

አዲሱ የወያኔ ካርታና «የህዳሴው» ግድብ ግንባታ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ እንዲሆን የተፈለገበት ሚስጥር – Achamyeleh Tamiru
አዲሱ በብሔራዊ ቴሌቭዥን የተዋወቀሙ ወረድ ብሎ የሚገኘው ካርታ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ከትግራይ ክልል ጋር አዋስኖ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ደግሞ ከጋምቤላ ክልል ጋር ድንበርተኛ ያደርጋል።
ይሄ ከስር የሚገኝው ካርታ ወያኔ «የህዳሴ ግድብ» እያለ የሚያንቆለጳጵሰውን የኃይል ማመንጫ ግድብ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ፤ ያውም ከሱዳን ድንበር አርባ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አደገኛ ቦታ ላይ፤ ለምን ለመገንባት እንደወሰነ እስካሁን ድረስ ሳይፈታ የቆየውን እንቆቅልሽ በግልጽ የሚፈታ ይመለኛል።
ወያኔ መነሻውን አይረሳም። የመለስ ራዕይ ኢትዮጵያን በማራቆትና በመዝረፍ የ1968ቱን የወያኔ ማኒፌስቶ ወደ ተግባር በመለወጥ የታላቋ ትግራይን ሪፑብሊክ መመስረት ነው። በነገራችን ላይ ዛሬ የትግራይን ሪፑብልክ መመስረት ህጋዊ መብት ነው። ወያኔ ባሻው ሰዓት አንድም ጥይት ሳይጮህ አንቀጽ 39ን ተግብሮ የትግራይን ሪፑብሊክን መመስረት ህገ መንግስታዊ መብቱ ነው። ከታች ያለው ካርታ ለታላቋ ትግራይ ምስረታ የሚሆን መሬት ለማግኘት ሲባል የትግራይን ክልል ከቤንሻንጉልና ከጋምቤላ ክልሎች ጋር በማስተሳሰር የአዲሷን የትግራይ ሪፑብሊክን መሰረት ጥሏል።
ባጭሩ ይሄ አዲሱ የወያኔ ካርታ የታላቋ ትግራይ ምስረታ ጫፍ እንደደረሰና የህዳሴው ግድብም ቤንሻንጉል ጉሙዝ ውስጥ [ከሱዳን ድንበር አርባ ኪሎ ሜትር በሚገኝ ቦታ ላይ] ለምን ግንባታው እንዲካሄድ ወያኔ እንደወሰነ፤ የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅም ግድቡ ለትግራይ ሪፑብሊክ ዋነኛ የሀይል ምንጭ እንዲሆን በሚገባ ተሰልቶ ወደ ግንባታ እንደተገነባ ከበቂ በላይ መልስ የሚሰጠን ይመስለኛል። በሌላ አነጋገር ታላቁ የህዳሴ ግድብ ቤንሻንጉል ላይ እንዲገነባ የተፈለገው የታላቋ ትግራይ ሪፑብሊክ የኃይል ምንጭ እንዲሆነ ስለተፈለገ ነው። የግድቡን የግንባታ ቦታ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሆን የመረጡ ሰዎች በአዕምሯቸው የትግራይ ሪፑብሊክን መመስረት አይቀሬነት እያሰቡ ያደረጉት ነው።
ትንቢተ ኤርምያስ [Kalkidan Legesse] በሁለት ወር ውስጥ በኢቲቪ ተፈጸመ
ባለፈስ ሰሞን ኤርምያስ ለገሰ ዋቅጅራ የወያኔን የወደፊት ህልምና «የታላቋ ትግራይ ሪፑብሊክ» ምስረታ ፕሮዠን አስመልክቶ በኢሳት ቴሌቭዥን በመቅረብ በጥልቀትና በስፋት ተንትኖ ማቅረቡ ይታወሳል። ያኔ በካርታ አስደግፎ የነገረን የወያኔ የረጅም ጊዜ ህልም ሁለት ወር ሳይሞላው ዛሬ ተፈጽሟል። የህልሙ ፍጻሜም ወያኔ በብቸኝነት በሚቆጣጠረው አንድ ለናቱ «ብሔራዊ» ቴሌቭዥን ጣቢያ ታውጇል።
እነሆ ዛሬ «የአማራ ክልል» ተብሎ በወያኔ የሚተዳደረውና እንዲጠፉ የተፈረደባቸው ዜጎች መኖሪያ የሆነው የግፉዓን ምድር፤ ራሱ «የአማራ ክልል» መስተዳደር የሚባለው አካል የኢቢሲን 50ኛ አመት ድግስ ስፖንሰር ማድረጉን ለማስነገር በሰራው የቴሌቭዥን ማስታወቂያ ላይ ክልሉን ሲያስተዋውቅ ወረድ ብሎ የሚታየውን «የአማራ ክልል» ካርታ በብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ አሳይቷል።
በዚህ በአዲሱ የአማራ ክልል ካርታ መሰረት የአማራ ክልል ከሱዳን ጋር አይዋሰንም። ከሱዳን ጋር የሚዋሰነው ከትግራይ ክልል ጋር እንዲዋሰን የተደረገው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ነው። በካርታው መሠረት ከትግራይ ክልል ጋር እንዲዋሰን የተደረገው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከጋምቤላ ክልል ጋርም እንዲዋሰን ተደርጓል። አሁን ሲንቆለጳጰስ የከረመው የመለስ ራዕይ ግልፅ የሆነ ይመስለኛል። የመለስ ራዕይ ማለት ወያኔ በ1968 ዓ.ም. ባወጣው ማንፌስቶ ያቀደውን «ታላቋን ትግራይ» የመመስረት አላማ ከፍጻሜ የማድረስ ግብ ነው። ይህ ግብ ተፈጻሚ የሚሆነው የአማራን ህዝብ መሬት በመንጠቅ፤ ህዝቡን በመግደል፤ ለም መሬቱን ለሱዳን አሳልፎ በመስጠት፤በልዩ ልዩ ዘዴ አማራውን በማዳከምና በማጥፋት፣ሌሎችን ብሔረሰቦች ደግሞ እርስ በእርስ በማናከስና በመዝረፍ ነው።