ጩኸትን ወደ ተግባር መተርጎም የትግል ጽኑነትን እና በራስ መተማመንን በአላማ ጽናት ያማከለ መሆን አለበት::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ጩኸትን ወደ ተግባር መተርጎም የትግል ጽኑነትን እና በራስ መተማመንን በአላማ ጽናት ያማከለ መሆን አለበት::
#Ethiopia #Oromoprotests #Ethiopiaprotests #EthiopianoppositionParties
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ካለፉት ታሪኮቻችን በተባባሰ መልኩ በዚህ በሰለጠነ ዘመን በአምባገነኖች መዳፍ ስር ሆነን ለነጻነታችን እና ለመብታችን በመታገል ላይ መሆናችን እሙን ነው:: ትግላችን ግን ከአንድነት ይልቅ መራራቅን ;ከመቻቻል ይልቅ ልዩነትን;ከመከባበር እና ከመደማማጥ ይልቅ በኔ አውቅልሃለሁ የኔን መጽሃፍ ድገም በሚል ድርቀት እና መጠላለፍ ወዘተ በመሞላቱ ድል አይደለም ተስፋ ፈንጣቂነት እንኳን እየበራ ሲጨልም እያየነው ነው:: ፖለቲከኞች በነጻ አውጪነት ስም ሃሰትን አባዝተው ለእውነት የሚያካፍሉት የፖለቲካ ሂሳብ ሕዝብ በጭቆና ውስጥ እንዲወድቅ እና ዝም እንዲል ድምጹን እንዲውጠው ምክንያት ሆነዋል::
የነጻነት ታጋይ የለውጥ ሃይል ነን የሚሉ ሃይሎች ለሕዝብ ከመቆም ይልቅ በተባበረ ሕዝባዊ ክንድ ቆራጥ ከመሆን ይልቅ ሕዝብን አስተባብሮ ወደ ለውጥ ጎዳና ከማምጣት ይልቅ እርስ በርሳቸው ሲናቆሩ ለሚዋጉት የተቃራኒ ሃይል በራቸው ከፍተው በመስጠት እየኖሩ እንዳይኖሩ መደረጉ በራሱ የህዝብን የነጻነት ቀንዲል እንዲከስም መስመር ዘርግቷል::ያልበሰሉ ካድሬዎች እና እዚህ ግቡ የማይባሉ የፖለቲካ ሹምባሾች የትግልን ምንነት ሳያውቁ እና ሳይረዱ የስትራቴጂን ፍጥነት እና መለዋወጥ አሊያም የፖለቲካ ውዳሴው ሳይገባቸው እየተነሱ ትግላችን ትግላችን ብለው ቢደሰኩሩ የሚሰማቸው ከማጣታቸውም በላይ ላለመላላጥ በራሳቸው ዛቢያ ሲፈራገጡ ይኖራሉ::
የትግልም ምንነት እና የአላማ ጽናት ያልገባቸው በየድህረገጹ እና በየፓልቶኩ የተኮለኮሉ የአላማ ጽናት እና የራስመተማመን ያጠራቸው የምላስ ሸርተቴዎች አንድ ሰው በፓልቶክ ተናገረ አሊያም በድህረገጽ ጻፈ በሚል ብቻ አላማና ግባቸው ከሚተቹት እና ከሚያማርሩበት ሰው ጋር አንድ ሆኖ እያለ የጋራ ጠላታቸው ላይ ከመዝመት ይልቅ የራሳቸውን ሰው ሲኮረኩሙ እና ትግላችን ተዳከመ እያሉ ሲያፏጩ ይስተዋላሉ:: የአላማ ጽናት እና በራስ መተማመን ካለ ትግል አይዳከምም :: አላማህን ይዘህ ወደፊት መገስገስ ከቻልክ ማንም አያሸንፍህም::ምናልባት ብትገዳገድ እንኳን እንዴት ቀጥ ብለህ ለመቆም አስብ እንጂ በሌሎች ላይ አትላከው::አንተ መስራት የምትችለው በራስህ ስትተማመን ነው::መታገል ሲደክመን አሊያም ስንሰላች በሰዎች ላይ ሰበብ እየፈጠሩ ከማላከክ የጋራ ሃይል አስተባብሮ ከድል መድረስ የሚቻለው በትግል ጽኑ ሲሆኑ በራስ መተማመን ሲኖር እና ለአላማ ጽናት ጠንክሮ ሲሰራ ብቻ ነው::ስለዚህ ትግል ጽኑነትን እና በራስ መተማመንን በአላም ጽናት ያማከለ መሆን አለበት እላለሁ::
#MinilikSalsawi
=== ይህን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር ልብ የሚል ካለ በትግል ጽናት ለአላማው ግቡን መምታት ይሰራል:: ===
“በሚሰሩት እና በሚጮሁት መካከል ያለው ሁኔታ inversely proportional ነው። ጯሂዎች ብዙ ሆነው የሚሰሩት ሰዎች ጥቂት ናቸው። ጯሂዎች ሳይሆን በተግባር የሚይዙት ሰዎች እንዲበዙና ትግሉን እንዲይዙት እናድርግ” … (ዶ/ር ብርሃኑነጋ )
“ወያኔ በወሬ አይወድቁም። በትግል ብቻ ነው የሚወድቀው። ለትግል ያመረረ ማህበረሰብ፣ ዲሲፕሊንድ የሆነ thinking ፣ ቁጭ ብሎ መሬት ያለውን ገምግሞ፣ ምን ማድረግ ነው የምንችለው የሚል ጠንካራ አስተሳሰብ የሚጠይቅ ነው” … (ዶ/ር ብርሃኑነጋ )