በአዲስ አበባ የበሽታ ወረርሽኝ ተከሰተ ‪አራት‬ ሰዎች ‪‎መሞታቸው‬ መንግሥት ያመነ ቢሆንም የሟቾች ቁጥር ከዚህ እንደሚበልጥ ይገመታል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በአዲስ አበባ የበሽታ ወረርሽኝ ተከሰተ

አራት‬ ሰዎች ‪‎መሞታቸው‬ መንግሥት ያመነ ቢሆንም የሟቾች ቁጥር ከዚህ እንደሚበልጥ ይገመታል።

የበሽታው መተላለፊያ መንገድ የአጭር ርቀት የትንፋሽ ልውውጦችና የአፍንጫ ፈሳሽ ንክኪዎች ሲሆን የበሽታው ምልክቶችም እንደ ማንኛውም ጉንፋን ቢሆኑም ጠንከር ያሉ ሊሆኑ ይችላሉ።

ወረርሽኝ እ.ኤ.አ. ከ2009 ጀምሮ በአዲስ መልክ በሰወች ላይ የመጣ ሲሆን በወቅቱ በአለም ጤና ድርጅት አለም አቀፍ ወረርሽኝ ተብሎ ታውጆ ነበር፡፡

በአለም ላይ በአመት 3-5 ሚልየን ሰወች በወረርሽኙ የሚጠቁ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ወደ 500ሺህ ያህሉ ለሞት ይዳረጋሉ።

ይህ በሽታ ኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ ሲሆን በተለምዶ የአሳማ ጉንፋን በሽታ ተብሎ ይታወቃል።

‪‎የመከላከያ‬ መንገዶቹም እንደ ማንኛውም ጉንፋን በማስነጠስ ወቅት መጠንቀቅ እና እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ እረፍት ማድረግና ብዙ ፈሳሽ መውሰድ፤ ህመሙ ከተባባሰ የህክምና እርዳታ ማግኘት ያስፈልጋል።