ጋብ ብሎ የነበረው የኦሮሚያ ክፍለ ሃገር ተቃውሞ አገርሽቷል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ጋብ ብሎ የነበረው የኦሮሚያ ክፍለ ሃገር ተቃውሞ አገርሽቷል::
#Ethiopia #Oromoprotests #EPRDF #OPDO #Miniliksalsawi
Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – የወያኔው አገዛዝ በቁጥጥር ስር አውየዋለሁ ሲለው የነበረው እና ባለፉት ወራቶች በተከታታይ ሲካሄድ የነበረው የኦሮሚያ ክፍለ ሃገር ተቃውሞ በተለያዩ አከባቢዎች አገርሽቶ መዋሉ ታውቋል::
[youtube http://www.youtube.com/watch?v=77bSm45sbZo]
በዛሬው እለት በወሊሶ በቡለሆራ በጀልዱ በኑኑቆምባ እና በተለያዩ አከባቢዎች ተቃውሞ የተሰማ ሲሆን በተለይ የአላሙዲን የወርቅ ማእድን መፈለጊያ እና ማምረቻ በሚገኝበት በቡሌሆራ ዙሪያ በከፍተኛ ደረጃ ተቃውሞ ሲሰማ መንገድ ሲዘጋ የዋለ ሲሆን የወርቅ ማምረቻው ለአከባቢው ተወላጆች ምንም ጥቅም ስላልሰጠ በወያነ እየተበዘበዝን ስለሆነ ለሕዝብ እንዲመለስ በማለት ተቃውሞው ሲሰማ የዋለ ሲሆን የወያነ ወታደሮች የገደሉትን የአንድ ወጣት አስከሬን በመያዝ ተቃውሞው ተፋፍሞ ውሏል::
በሌሎችም ከተሞች እንዲሁ ተማሪዎች እና የወያኔ ወታደሮች ተጋጭተዋል::በተማሪዎች ላይ ከሞት እስከ አካል ጉዳት መድረሱን የአከባቢው መረጃዎች ጠቁመው የቡሌሆራ ህዝብ ጊዜያዊ የአግአዚ ካምፕ እና የቡሌ ሆራን ግምሩክ ሙሉ በሙሉ አቃጥለውታል::እስከ ምሽቱ ድረስ ታቃውሞ እንደቀጠለ ይገኛል::
