የወያኔ ባለስልጣናት እና ጭፍሮቻቸው ከደሃው ጉሮሮ መንጠቁን ተያይዘውታል ኢትየጵያ ውስጥ ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንደ ብቃትና እንደ ሥልጡንነት እየታየ ነው፡፡
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ኢትየጵያ ውስጥ ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንደ ብቃትና እንደ ሥልጡንነት እየታየ ነው፡፡
#Ethiopia #EPRDFCorruption #Miniliksalsawi #Ethiopianoppositionparties
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናት እና ጭፍሮቻቸው ከደሃው ጉሮሮ መንጠቁን ተያይዘውታል ግን እስከመቼ የለውጥ ሃይሉ በመታገል ፈንታ እርስ በርስት እየተባላ የወያኔን እድሜ አሳልጦታል:: አገሪቷ ውስጥ ያለው የኑሮ ውድነት ወደላይ እንዲያሻቅብ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ የሙስና ጣርያ መንካት ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ አሳሳቢ መሆኑን መግለጽ ቀርቶ የእገሌን አገር ደረጃ አያክልም የሚለውን አባባል የኢትዮጵያ ሕዝብን እንደመናቅ ይቆጠራል፡፡በአሁኑ ወቅት ሙስና በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቷል፡፡ ባለጉዳይም ጉቦ ካልሰጠ ጉዳዩን እንደማያስጨርስ፤ ጉዳይ ፈጻሚም ገንዘብ ካላገኘ ጉዳይን ማስጨረስ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን በገሃድ በሚታይበት ደረጃ ላይ ነን፡፡ በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ፣ በአዲስ አበባ መስተዳድር፣ በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት፣ በአገር ውስጥ ገቢ፣ በጉምሩክ፣ በመንገድ ትራንስፖርት፣ በሆስፒታሎች፣ በኢሚግሬሽን፣ ወዘተ ጉዳይን ለማስጨረስ ጉቦ መስጠት የተለመደ ሆኗል፡፡
ጉቦ መስጠትም ሆነ መቀበል እንደ ብቃትና እንደ ሥልጡንነት እየታየ ነው፡፡ ጉቦ የማይቀበል የማይረባና የማይጠቅም ተብሎ የሚሰየምበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን እያንዳንዱ ሰው በሚገባ ያውቀዋል፡፡ እንደዚህ በመሰለ አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ባለንበት ወቅት ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ አሳሳቢ ደረጃ ላይ አይደለም ሲባል ምን ማለት ነው? መረጃው የተገኘውስ ከየት ነው? ከተበዳይ ወይስ ከበዳይ?ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዢዎች አነስተኛም ይሁኑ ትላልቅ የፕሮጀክት ጨረታዎች ያለኮሚሽን ክፍያ የተፈጸሙ ናቸው የሚል ጥናት ፍፁም ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡ ምንልክሳልሳዊበአሁኑ ወቅት በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚካሄዱ ግዢዎችና ጨረታዎች ሕጋዊነትን ለማስያዝ ብቻ የሚካሄዱ ካልሆነ በስተቀር፣ አስቀድሞ ከታቀደውና ከታለመው ሰው ወይም ድርጅት ውጭ ማንም እንዲገባ በማይፈቀድበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን የዋህ ሰው ሳይቀር በሚገባ የሚረዳበት ደረጃ ላይ እኮ ነን ያለነው፡፡
ከሀብታም ነጋዴዎች ጋር የሚያያዝ ከሆነ ቀድመው ችግሩን ለማወቅና ለመፍታት ከሚጥሩ ይልቅ ለግልግል በሚሯሯጡበት አገር ላይ እያለን፣ ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ዝቅተኛ ነው እንዴት ይባላል? በአሁኑ ወቅት ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የመንግሥት አመራሮች ድረስ በሀብታም ተፅዕኖ ሥር በወደቁበት፣ ጉቦ በመቀበል የአገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈው በሚሰጡበት፣ ሀቅን በገንዘብ በሚለውጡበት፣ በጠራራ ፀሐይ ብሉ ሌብልና ቪኤስኦፒ በካርቶን በሚጫንበት፣ የሰው ሕይወት በገንዘብ አደጋ ላይ በሚወድቅበት፣ ዓይን ያወጡ ሙሰኞች በሰፊው ሕዝብ ፊት ደረታቸውን ነፍተው ጉራቸውን በሚነፉበትና ኃይላቸውን የሚያሳዩበት ወቅት መሆናችን እየታወቀ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ አይደለም እንዴት ይባላል?
የመንግስት ባለስልጣናት የሙስና መንገዳቸውን ለማሳካት ሲሉ በመንግሥት ፖሊሲ፣ አሠራርና መመርያ ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሚመቻቸው ተደርጎ እንዲወጣ በማድረግ ላይ ናቸው ሲል ሙስና ኮሚሽን አማሯል።ትናንትና ለሀቅ፣ ለዲሞክራሲና ለአገራቸው ብልጽግና ሲሉ የወጣትነት ዕድሜያቸውን በረሃ የወጡ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውንና ጓደኞቻቸውን ቀብረው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱ ጀግኖች በሙስና ተነክረው ሀብታም ሥር በተንበረከኩበት ወቅት፣ የተለያዩ ድርጅቶች ቅጥረኛ በሆኑበት ወቅት፣ አሠራርና መመርያዎችን ጥሰው በኔትወርክ በተሳሰሩበት ወቅት፣ እርስ በራሳቸው እሳትና ጭድ ሁነው በማይተማመኑበት ወቅት፣ ለሕዝብ ህልውና ዋስትና በታጣበት ወቅት፣ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያሳስብ አይገባም ተብሎ እንዴት ይነገራል?
ከምንም ጊዜ በላይ እጅግ አሳሳቢ፣ ከአሳሳቢነቱ በላይም ጊዜ የማይሰጠውና ወረርሽኝ በሆነበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው፡፡ አንዳንድ ቦታ ላይም ሙሰኞች የሙስና መንገዳቸውን ለማሳካት ሲሉ በመንግሥት ፖሊሲ፣ አሠራርና መመርያ ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሚመቻቸው ተደርጎ እንዲወጣ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ወሬዎች በሚናፈሱበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው፡፡ አንዳንዱ ቅንጣት ጥፋት የሌለው ይመስል ከራባቱን አስሮ ‹‹ሙስናን እንዋጋ›› የሚለው ከበስተጀርባው ትልቅ ጥፋት ተሸክሞ ነው፡፡
እጅግ የሚያስፈራው ደግሞ ሙስና ከመስፋፋቱም በላይ ሙስናን የሚዋጋና እውነታው ገሃድ እንዲሆን ጥረት የሚያደርግ ወገን ያለአግባብ እየተበደለ ነው፡፡ ሙሰኞች በያዙት የሕዝብና የመንግሥት ሥልጣን ሀቅን ለመቅበር የሚችሉትን ያህል ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ አገሪቷን እጅና እግሯን አስሮ ለጅብ እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡ እኛስ ምን እየሰራን ነው ራሳችንን እንጠይቅ ነጻ ለመውጣት ከመታገል ይልቅ እየተኮራኮምን የራሳችን ባሪያዎች በመሆን በባዶ ሜዳ እየዛረጥን ስለምንገኝ ከዚህ ስህተታችን ተምረን ልዩነት በማቻቻል ታግለን በሕዝብ ትከሻ ላይ የተንሰራፋውን የወያኔ አገዛዝ እናስወግድ!!! #ምንልክሳልሳዊ
