ጃዋር ወጣቱ የፖለቲካ ስካር ፣ የ-ግለት እና የግለኝነት አብሾ ( ሄኖክ የሺጥላ )
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ጃ`ዋር ወጣቱ የፖለቲካ ስካር ፣ የ-ግለት እና የግለኝነት አብሾ ( ሄኖክ የሺጥላ )
< እንጀራውን > በተገፉ እና በተከፉ ሰዎች ታሪክ ላይ ያደረገ ሰው ፣ ህይወቱን በሰዎች መከራ ላይ የገነባ ሰው ፣ ኑሮውን ባጋጣሚ ለድምጽ አልባ እና አቅም አልባ ወገኖቹ ለታይታ በመቆጨቱ ፣ የድንቡሎ መና ሰው የመሆን አቅሙን የነጠቀበት ሰው ፣ ከሚያገኘው ቤሳ ጋ ፍቅር በመውደቁ ብቻ ሕዝባዊ መቆጨትን ፣ ወይም ለተጠቁ በጋራ መጮህን የግል ንብረቱ ሊያደርግ የሚያስብ ሞኝ ፣ስለምንም አይነት ምድራዊ ምክንያት ፣ ስለ ስብአዊነትም ሆነ ስለ አንድነት እና ፍቅር ልታስረዳው ፣ ልታስተምረው ወይም ልትመክረው አትችልም ። እኔ ብሎ እየኖረ ለእኛ ነው የማለቅሰው የሚል ጠባብ ፣ ራሱን ከተበተበበት የግለኝነት ውል አልባ ቋጠሮ ፣ ከኔ-ወዲያ ላሳር በሚለው ምስኪን ነብሱ ውስጥ ሁሌም የምታየው ትንሽነቱን ብቻ ሳይሆን ፣ ተፈጥሮው ትልቅ ለመሆን ያልተፈጠረ ፣ ትልም አልባ ፣ ሕልም አልባ ጭንጋፍነቱንም ጭምር ነው ። እንዲህ አይነት ሰው ምንምን ወደ ፊት የመግፋት አቅም የለውም ፣ ግን ደሞ እንደ ጨጎጊት የመንፈስን መቀነት መያዙ ፣ እንደ እሾህ የሚራመዱ እግሮችን መውጋቱ ፣ ማድማቱ እና ትንሽም ቢሆን እንከን እና ስንካር መሆኑ ግልጽ ነው ። ምክንያቱም ራሱን ትልቅ ለማድረግ ፣ ከፊት ሆኖ ለመታየት እና ለመግነን ማናቸውንም አይነት ክፋት ከመፈጸም ልቡ ተው የሚለው አይነት ስላልሆነ ፣ ምክንያቱም የጆሮ ግንዱ የተሸከመው የስጋ ቅጠል፣ ከራሱ ሌላ ማናቸውንም አይነት ድምጽ ለማዳፈን የተሰራ የመስሚያ ቅንቡርስ እንጂ የማዳመጫ አካል ስላልሆነ ።
ጃዋርን ሳስብ ከላይ የገለጽኩት ሁሉ ገልጾ የማይጨርሰው አይነት ሰው እንደሆነ እረዳልሁ ። በጃዋር ልቦና ውስጥ ሀገር የሚባል ነገር የለም ፣ ሕዝብ የሚባል ነገር የለም ፣ ወገን የሚባል ነገር የለም ! ለጃዋር አማራ ፣ ኦሮሞ ፣ ጉራጌ ፣ ወዘተ የሚባል ኢትዮጵያዊ የለም ፣ በጃዋርኛ ፖለቲካ ውስጥ የምትመለከተው ጃዋርን ብቻ ነው ። የጃዋር ቁባ ነው የሚያበራው ፣ ኦሮሞነት ከጃዋርነት ቀጥሎ የሚመጣ ፈሊጥ ነው ። በመሰርቱ ጃዋር ትልቅ የማንነት ቀውስም ያለበት ሰው ነው ። ይህንንም ስል ጃዋር እራሱን ለራሱ ሲል ክዶ ያመነ ፍጥረት ነው ። ምን ማለቴ ነው ? ሃሳቡን በአዲስ መስመር እናብራራው
ጃዋር ከመንዜይቱ እናቱ እና ከ ኦሮሞው አባቱ የተወለደ ባለ ውብ ቀለም ኢትዮጵያዊ ነበር ። ምን ያረጋል ነበር ብቻ ሆነ ። ጃዋር ንጉስ ዔድፐስን ይመስለኛል ( ልዩነቱ ጃዋር እናቱን ገሎ አባቱን ማግባቱ ካልሆነ በስተቀር !) እንጂ ታሪካዊ ስሜታቸው አንድ አይነት ነው ። አባቱን ገሎ እናቱን ያገባ ሰው ትልቅ ሀጥያት ሰራ ልንል እንችላለን ፣ እናቱን ገሎ አባቱን የሚያገባ ወንድ ግን ምን ሊባል እንደሚችል እኔ አላውቅም !
ጃዋርን በተለያየ የፖለቲካ መተጣጠፍ ውስጥ ነው የማውቀው ። ከዚህ በፊትም ገልጨዋለሁ ፣ የጃዋር መንፈስ የቀንድ አውጣ አይነት ነው ፣ ኮሽ ሲል የሚጠቀለል ፣ ጭጭ ሲል የሚዘራጋ ። ጃዋር ብልጥ ነው ፣ ብልህ ግን አይደለም ! ብልጠት ደሞ ከአንድ ቤተሰብ የማያልፍ ታሪክ ያለው አቋቋም ነው። ለዚህም ነው የታሪክ አምድ ዋልታዎቹን የገነባው በብልሆች ጥበብ እንጂ በብልጦች ማንነት ላይ ያልሆነው ።
ጃዋር ያልሆነውን ሆኖ ለማያውቀው ነገር የቆመ አጋፋሪም ይመስለኛል ። ምሳሌ ልጥቀስ
የኢትዮያ ሙስሊሞች ( በይበልጥም ሙስሊም ኦሮሞዎች ) የአቢሲኒያን የፖለቲካ የበላይነት መያዝ እንዳለባቸው የሰበከበትን አንድ ቪዲዮ አስታውሳለሁ ። ግን ጃዋር ማን ነው ? እስልምናን እሱ የሚቆረቆርለትን ያህል ያውቀዋል ወይ ? ይህንን አጠገቡ ያሉት ሰዎች ነገ ከነገ ወዲያ ወጥተው እንደሚመሰክሩ አልጠራጠርም ። አንዳንድ ግልጥ ማስረጃዎችን ግን ለመጠቆም እወዳለሁ ። ጃዋር የራሱ ቤት ( ማጀቱ ) እስልምናን ያውቃል ወይ ? መልሱ አጭር ነው አያውቅም ። ከላይ እንደገለጽኩት ጃዋር ለእስልምና የቆመው በእስልምና በኩል መቆም እንደሚችል ስለሚያውቅ ብቻ ነው ! ጃዋር ለኦሮሞውጭ የቆመው ፣ በኦሮሞውጭ ስም መቆም እንደሚችል ስለሚረዳ ነው ። በጃዋር ዓለም ከጃዋር ፊትም ሆነ ከጃዋር ወዲያ ማንም የለም እሱና እሱ ብቻ ።
ዛሬ በኢትዮያ በሸዋ እና በወለጋ ኦሮሞዎች የሚደረገው ትግል የጃዋር ትግል የሆነው ስላመነበት አይደለም ፣ አጋጣሚ ስለፈጠረለት እንጂ ። አንድ የኦሮሞ ሕዝብ መረገጥ የሚቆጨው ሰው በምን አይነት ሂሳብ ነው የኦሮሞ የማንነት መሰረት የሆነው የኦሮምኛ ቋንቋ በሌላ ሚዲያዎች ሲነገር ሲሰማ ሊከፋው የሚችለው ? እንዲህ ማለት ነው
ለምሳሌ ጃዋርየቀዶ ጥገና ሀኪም ቢሆን ፣ ከበሽተኛው ሆድ ዕቃ ውስጥ ያለውን በአድ ነገር ለማውጣት የበሸተኛውን ሆድ ዕቃ ከፍቶ እንደጨረሰ በሽተኛው ራሱ የቀዶ ጥገና ሀኪም መሆኑ ሲረዳ ፣ ይሄማ ቢድን ስራዬን ስለሚቀማኝ ቢሞት የሻላል ብሎ የሚል አይነት ሀኪም ነው ። በጃዋር ውስጥ ከጃዋር ሌላ ማንም የለም ። ሊኖርም አይችልም ! ጃዋር ወጣቱ የፖለቲካ ስካር ፣ የ-ግለት እና የግለኝነት አብሾ። ሕዝብ ሞኝ ነው ያሉ ቂሎች ዛሬ የት እንዳሉ አለማወቅህ ግን ያሳዝነናል ።