አሰብን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ….??? Kidane Amene


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አሰብን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ….???Kidane Amene

==============================

Kidane Amene's photo.

ሰሞኑን RED SEA AFAR DEMOCRATIC ORGANIZATION የተባለ ፀረ ሸዓብያ ድርጅት በሸዓብያ ስላላ አባላት ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰዱን እየሰማን ነው፡፡ በኔ በኩል ይበል የሚያሰኝ እርምጃ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያንም ታሪካዊው የባህር በራችን ለማስመለስ ከፀሓይ በታች ያሉ ሁሉም አመራጮች አሟጠን የመጠቀም ሀላፊነት ያለብን ቢሆንም እስካሁን ባለኝ የግል ጥናት መሰረት የሚከተሉትን አማራጮች አሉን:-

 

1. INTERNATIONAL LAW በመጠቀም፡፡ በታሪክም በህግም አሰብ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ አካል ስለሆነ አለም አቀፍ ህግ ተጠቅመን ብሄራዊ ጥቅማችንን የምናስከብርበት ሰፊ እድል እንዳለ እንደነ ዶ.ር ያዕቆብ ሀ/ማርያም የመሰሉ ዓለም አቀፍ የህግ ሙሁራን ያሳስባሉ፡፡ በሙሁራኖቻችን አንደበት መሰረት ሚያስፈልገው 4 ኪሎ ቤተመንግስት አሰብን ለመመለስ የቆረጠ ሀላፊነት የሚሰማው መንግስት መኖር ብቻ ነው፡፡


2. የአልጀርሱ ስምምነት በመሰረዝ ሌላ አዲስ ዲፕሎማሲ መጀመር፡፡ የአልጀርስ ስምምነት ቅኝ ግዛት ውሎች መሰረት ኣድርጎ የተፈፀመ ስለሆነና የቅኝ ግዛት ውሉቹ ደግሞ ጣልያን ራሷ በ1935 ኢትዮጵያ በመውረር ስላፈረሰችው ኢትዮጵያ ምኒልክና ጣልያን መካከል በ1902፣1903 ና በ1908 በተደረገ ስምምነት የመገዛት ህጋዊ ግዴታ ስለሌለባት የአልጀርሱ ስምምነቱ ፈርሶ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት የምትሆንበትን ኣዲስ ድርድር በመክፈት ብሄራዊ ጥቅምዋን ማስከበር፡፡


3. ኤርትራ በሪፈረንደም (ሪፌረንደም ሲባል እንደትላንቱ ”ነፃነት ወይስ ባርነት” የሚል ሳይሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የተከተለ እውነተኛ ሪፈረንደም ማለቴ ነው)… ወይም በኮንፈዴሬሽን የኢትዮጵያ አንድዋ የፌዴራል አካል ማድረግ፡፡

4. በአሰብ የሚኖር የአፋር ህዝብ በሪፈረንደም እድሉ እንዲወስን በማስቻል፡፡ በአሰብና በአካባቢው የሚኖሩ ህዝቦች አብዛኞቹ አፋሮች እና ኢትዮጵያውያን ስለሆኑና “አይደለም እኛ ግመሎቻችን የኢትዮጵያ ባንዲራ ያውቁዋታል” የሚል እምነት ስላላቸው በሪፈረንደም ወደ ኢትዮጵያ የሚቀላቀሉበት እድል ማመቻቸት፡፡ አፋሮቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሮው ወንድማቸው አንድ መሆን ስለሚፈልጉ የራሳቸውን እድል በራሳቸው እናዲወስኑ የዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ እድል ከሰጣቸው (ልክ ክሪምያ ወደ ራሺያ ንደተቀላቀለቺው) እነዚህም ያለ ምንም ጥርጥር ኢትዮጵያ ኢንደሚመርጡ ግልፅ ስለሆነ ይህንን ዘዴ መጠቀም ሌላው አማራጭ ነው፡፡


5. ከላይ የተዘረዘሩ አማራጮች ትርጉም ያለው ለውጥ ካላመጡ በኤርትራ ያሉ እንደ RED SEA AFAR DEMOCRATIC ORGANIZATION ዓይነት ሸዓብያን የሚወጉ ተገንጣይ ድርጅቶች በፋይናንስም በጦርም በመርዳት ተገንጥለው ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው አብዛኛው(ማጆሪቴ) አፋር እነዲሰምሩ በማድረግ አሰብና አካባቢው የኢትዮጵያ አካል ማድረግ ሲሆን፡፡


6. ከ 1 እሰከ 5 ያሉ መንገደች ካልሰሩ የመጨረሻውና ከባድ መስዋእት የሚጠይቅ … ነገር ግን መደረግ ያለበት አማራጭ በጦርነት መመለስ ነው፡፡ ስለዚህ WAGING WAR አይቀሬ ይሆናል:: ምክንያቱም አሰብ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የፀጥታና የደህንነት ብሎም የህልውና ጉዳይ ስለሆነ የተከፈለ ተከፍሎ በባሌም በቦሌም የባህር በሩ መምጣት አለበት፡፡

 

በስዕሉ እንደምታዩት ቀዩ ካርታ አሰብና አካባቢው የሚያመለክት ሲሆን ወደፊት በትግላችን እሱን መመለስ ግድ ይሆናል፡፡

Kidane Amene's photo.