የኦሮሞዎችን ተቃዉሞ በተመለከተ ዶር ብርሃኑ የተናገሩት


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኦሮሞዎችን ተቃዉሞ በተመለከተ ዶር ብርሃኑ የተናገሩት – ግርማ ካሳ

ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በዋሺንገትን ዲሲ ባደረጉት ንግግር በኦሮሚያ በተነሳው እንቅስቃሴ ዙሪያ 4 ነጥቦችን አንስተው ትምህርት ሰጪ ሃተታዎችን አድርገዋል።

ሲጀምሩ በኦሮሚያ የተደረገው ነገር ለርሳቸው emotional እንደሆነ ነበር የገለጹት። “ሕጻናት፣ እርጉዞች፣ አሮጊቶችን መግደል፣ መርገጥ ….. ፣ እርሱ ለማወገዝ ኢትዮጵያዊ መሆን የለብንም። ሶሪያ ላይ ይሄ ነገር ሆነ ብለን እናዝን የለም እንዴ ? “ ያሉት ዶክተሩ፣ ከምንም ነገር በላይ ፣ ሌላ ስሌቱን ቀርቶ፣ የሰው ልጆች ናቸውና፣ በምንም መልኩ፣ ማንም ያድርገው መወገዝ እንዳለበት ነው የገለጹት።

“በወገኖቻን ላይ መሆኑ ደግሞ፣ የሚጥልብን እዳ አለ። ከከንፈር መምጠት ወዲያ ማድረግ ያለብን ነገር አለ። ወገኔ ከሆነ፣ ዝም ብዬ ከንፈር መምጠት ከሆነ፣ ምኑ ላይ ነው ወገንንቱ ። ይሄ ነገር እንዲቆም ማድረግ ያለብንን ሁሉ ማድረግ አለብን” ሲሉ ነው ያሰመሩበት።

በመቀጠል በሁለተኛነት የችግሩን መንስኤ መረዳት አንደሚያስፈለግም ያስረዱት ዶር ብርሃኑ የተቃዉሞው መንስኤ ማስተር ፕላኑ እንደሆነ ገልጸው፣ ከማስተር ፕላኑ ጀርባ ግን ጥያቄው የመሬት ጥያቄ እንደሆነ ነው ለማሳየት የሞከሩት። “የማስተር ፕላኑ ጥያቄ ማስተር ፕላን የሚለው አውጥታችሁ ብታዩት፣ የመሬት ነጠቃ ነው” ነበር ያሉት።“የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ተባረዋል፤ ለወያኔ ሃብታሞች ቦታ ለመልቀቅ” ሲሉ፣ ይህ የመሬት ጥያቄ፣ ከማስተር ፕላኑ በፊት በአዲስ አበባ የነበረ ችግር እንደሆነም አስረድተዋል።፡በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በጋምቤላ 300 ሺህ ወገኖች በላይ ከሚኖሩበት ቦታ እንደተባረሩ፣ ለስኳራ ምርት ተብሎ ፣ በአፋር ክልል በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች መንጋቸውን የሚያሰማሩበት መሬት እንደተነጠቁ በመግልጽ፣ ችግሩ ትግራይ ዉስጥም ጨምሮ በሁሉም ቦታቸው እንዳለ ነው ያስረዱት። ስለትግራይ ሲናግሩ “ በትግራይ በራያና አዘቦ የዚያ አካባቢ ለካድሬዎች ቤት ለመስራት ድሃው አፈናቅለዋል፤ በመቀሌ የአፓርታይድ መንደር የሚባል አለ አይደለም እንዴ ? ድሃዉን አባራው እነርሱ የሰሩበት ? “ ነበር ያሉት።

የመሬት ነጠቃው ችግር በሁሉም ቦታ ያለ፣ የአንድ ብሄረሰ ጥያቄ ሳይሆን የመደብ ጥያቄ እንደሆነ የገለጹት ዶር ብርሃኑ በሌሎች ቦታዎች ያለውና በኦሮሚያ ያለው ልዩነቱ አንድ ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል። እርሱም፣ ኦሮሞዎች ለመታገል መወሰናቸው ። “እነርሱ ተነስተው፣ መንገድ ላይ ወጥተው ተቃዉመዋል። እኛ ይሄን የማንደገፈው ለምንድን ነው ? ቅናት ነው ? እንደ ጥያቄ ያነሱት የመሬት ጥያቄ፣ ይሄን ትግል እንድንደግፈው እንጂ እንድናቀወመው የሚይደርግ አይደለም” ሲሉም ተቃዉሞ መደገፍ እንዳለበት አጥንክረው አሳስበዋል።

“ጥያቄ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ነው” ያሉት ዶር ብርሃኑ፣ “ አሁን ያለውን ስሪት፣ ማንንም ከማንም ቢታ ለማስነሳት የሚያስቸል ስሪት ነው ያለው። መሬት የመነግስት ነው ስለሚሉ በፈለጉ ጊዜ ምንንም ሊያስነሱ ይችላሉ ሲሉ ችግሩ ከመሬት ባለበትነት ጋር እንደሆን አስረድተዋል።

በሶስተኛ ደረጃ ዶር ብርሃኑ ሌላውም ማህበረሰብ ሙሉ ለሙሉ ልባችን ሰጥተን ለምን የኦሮሞዎችን እንቅስቃሴ መደገፍ እንዳልተቻለ ሲያስረዱ፣ “ችግሩ የማንነት ፖለቲካ የፈጠረብን ስሜት አለ” በማለት ነበር።
የግላቸው እንጂ የደርጅታቸው አቋም እንዳለሆነ የገለጹት ዶር ብርሃኑ “ዘላቂ የመረጋጋት እና እዉነተኛ ዲሞክራሲ ከመፍጠር አኳያ የማንነት ፖለቲካ አይጠቅመን ብቻ ሳይሆን በዜግነት ላይ ወደ ተመሰረት ፖለቲካ ነው ዘላቂ መረጋጋት የሚሰጠን ብዬ ነው የማምነው” ነበር ያሉት። “ በማንነት ፖለቲካ ላይ ተመሰርቶ የተረጋጋ አገር መፍጠር አይቻልም ብዬ አማናለሁ።የወደፊቷ ኢትዮጵያን ስናስብ ከዚህ ከማንነት ፖለቲካ እንዴት እንደምንወጣ ማሰብ አለብን” ሲሉም አክለዋል።

“ይሄ ስንል ግን የማንነት ፖለቲካ ለምን እንደተፌጥረ መረዳት አለብን” ያሉት ዶር ብርሃኑ አሁን ያለዉን የማንነት ፖለቲክ እንዲሁ እንዳልመጣ በመረዳት በጊዜያዊነት accommodate በማድረግ በሂደት ማሻሻል እንደሚገባም ለማሳየት ሞክረዋል። “የማንነት ፖለቲካን ከዚህ በፊት የነበረው ችግር ያመጣው በመሆኑ ፣ በማንነት ፖለቲካ ዉስጥ ያለውን ማህበርሰብ እንዴት ነው የምንቀይረው ካለን የሽግግር ስትራቴጂ ያስፈልገናል” ብለዋል ዶር ብርሃኑ።

ስለኦሮሞዎች እንቅስቃሴ ዶር ብርሃኑ ሲትነትንኑ ከአክራሪነት የጸዳ እንደሆነ፣ መገንጠል የሚለው ጥያቄ እዚህ ትግል ዉጥ እንደሌለ፣ ወያኔዎች እየተነኩስትም፣ የሌሎችን ብሄር ሰዎች attack ለማድረግ ሙከራ እንዳልተደረገና የኦሮሞ ቡድኖች ሌላው ኢትዮጵያ እንዲቀላቀላቸው ለመጀመርያ ጊዜ ጥሪ ማቅረባቸው በመጥቀስ ነበር በጎነቱን አጉልተው ያሳዩት።

በአንጻሩም “የዚያኑ ያክል ግን፣ በኦሮሚያ የሚደረገው ትግል ደግፎ ፣ ሌላው አካባቢ ያለው ባለመነሳቱ የፈጠረው ችግር አለ” ሲሉም ሌላ ኢፌክት በተቃራኒው እንዳለ ገልጸዋል።

ከኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በጋራ ለመንቀሳቀስና ፣ የማንነት ፖለቲካ ትራዚሽናል በመሆኑ፣ አሁን ትግሉ ለማቀናጀት፣ በተግባር የተጀመሩ ስራዎች በቶሎ መጀምር እንዳለባቸው የገለጹት ዶር ብርሃኑ “የአክራሪ ዱላ ተፈርቶ ትግል አይቆምም፤ የያዝነው የአገር ጉዳይ ነው” ነበር ያሉት። “ሰዎችን ማስጮህ ቀላል ነው። ማህበረሰብ አሰባስቦ ዉጤት ማምጣትት ከባድ ነገር ነው” ያሉት ዶር ብርሃኑ ከኦሮሞ ሞደሬት ሃይሎች ጋር በመሆን፣ እዉነተኛ ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር ለመገንባት ፍላጎት አላቸው ብለው ከሚያምኗቸው ጋር ዉይይቶች መጀመሩን ለተሰብሳቢው ገልጸዋል።