አዲስ አበባ ለምን ዝም አለች (Eyasped Tesfaye)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አዲስ አበባ ለምን ዝም አለች
~~~~~~~~~~
<<ቅድስት ብዙ ግዜ እያመሸች ትሰራልች። አንድ ቀን ለአይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር ከስራ ወጥታ ወደምትኖርበት የጨረቃ ቤቶች ወደሚበዙበት መንደር ታዘግማለች። ጓደኛዋ ጋር ደውላ ስራ በማምሸቷ ምክንያት ልታገኘው እንዳልቻለች በማውራት ላይ ሳለች ሁለት ጎረምሶች ስልኳን በጉልበት ነጥቀዋት ሮጡ…..ቅድስት ጮኽች….ሌባ ሌባ ሌባ ኡኡኡኡኡ
ማን ትሆን የፈረደባት በዚህ ምሽት የምትጮህ? ማንም ከቤቱ አልወጣም እየሰማ ጭጭ። ራሱ ላይ ስላልደረሰ ይሆን?>>
~~~~~~~~~
<<የቀበሌ ሹማምንቱ ከፌደራል ፓሊስ እና ከአፍራሽ ልዩ ግብረ ሀይል ጋር በመሆን የጨረቃ ቤቶቹን ለማፍረስ ሽር ጉድ እያሉ ነው። ከወለደች 4ኛ ቀኗን የያዘችው እመጫትን ጨምሮ ማረፊያ መጠጊያ የሌላቸው አዛውንቶችና ህፃናት ቤታቸው ሊፈርስ ነው። ይህ ሲሆን ቤቱ የሚፈርስበት ህዝብ ቆሞ ከመመልከት ውጭ ምንም አላደረገም። ለቅድስት ጩኸት ምላሽ ያልሰጠው በራሱ ስላልመጣ ነው እንል ይሆናል….አሁንም ራሱ ላይ ስላልደረሰ እንል ይሆን?>>
~~~~~~~~~
<<ከወር በፊት ነው…..የተማሪዎቹን ተቃውሞ ገበሬው መቀላቀሉ በጣም ደስ የሚል ነው አልኩት በማለዳ ያገኘሁትን አንድ ወዳጄን።
ትቀልዳለህ እንዴ ገበሬው እህል አልክም ወደከተማ ቢል ምን ሊውጠን ነው? እነ ጃዋር ምንም ለውጥ ላያመጡ ነገር ዝምብለው እሳት ያያይዛሉ። እዚያው ተማሪዎቹ እንደፍጥርጥራቸው አለኝ። ይህን ያለኝ ሰው ኦሮሞ መሆኑ ደግሞ የበለጠ ገርሞኛል።>>
~~~~~~~~~
<<እረ ተዉ እረ ተዉ ሰልፍ ጥሩን….. ቆይ ሁላችንም እስክናልቅ ነው እንዴ ዝምብላችሁ የምታዩት??? ሌላኛው የአ.አ ወዳጄ በጣም በመብሰልሰል አንድ ቀን ሳይሆን በተደጋጋሚ የሚጠይቀኝ ጥያቄ>>
~~~~~~~~~~~
<<~እኔ ምልህ ኦሮሚያ ላይ የነበረው ተቃውሞ ቆመ አይደል?
~እረ አልቆመም እንደውም ተፋፍሟል
~ ምን ሚዲያ የለን በምን እንሰማለን ብለህ ነው>>
~~~~~~~~~~~~~
የግርምሽንና የአቤኖን ጭቅጭቅ አይቼ ወዳጆቼን ጠየኳቸው…. የአ.አ ህዝብ ለምን ዝም ይላል?
~ ሆዳም ስለሆነ ነው አለች አንዷ
~መረጃው ስለሌለው ነው አለ ሌላው
~ካድሬው እና ሌላውን መለየት ይከብዳል አብረኸው ስታወራ ቆይተህ ጠቁሞ የሚያሳስርህ አስተኳሽ ይበዛል…
እናም የአ.አ ህዝብ እንደ ገጠር ከተማ ህዝብ አይተማመንም…..አለ ሌላው
~በራሱ ካልመጣ ምንም አይመስለውም ግዴለሽ ነው….ሌላኛዋ
~~~~~~~~~~~~~
እኔ ደግሞ በግሌ ተቃዋሚ ነን የምንለው እና አክቲቪስት ነን የምንለው ሰዎች ድክመት ይመስለኛል። ቢያንስ አንድ ሰልፍ ጠርተን ህዝቡ ይወጣል አይወጣም የሚለውን መቼ ሞከርነው???
ዶ/ር መራራ በሰማያዊ ቢሮ ተደርጎ የነበረው ውይይት ካለቀ በኃላ ወደቤታቸው እየሸኘናቸው ጓደኛዬ ጋሻው ስለ ሰልፉ ጠየቃቸው…… “አዲስ አበባ ውስጥ ሰልፍ ቢደረግ ኦሮሞውና አማራው በአንድ ላይ የሚወጣበት በመሆኑ ኢህአዴግ ይህ እውን እንዳይሆን የማያደርገው ነገር የለም” አሉ….. ዶ/ር መራራ ያሉት በሙሉ እውነት ነው። አሁንም ያለውን መከላከያ እና መረብ ሁሉ በጥሰን ትልቅ ትዕምርታዊ ትዕይንት አ.አ ውስጥ ማድረግ ያስፈልገናል።
Till then there is no need of raising divisive issues even if what we are saying is true. With respect!

Eyasped Tesfaye's photo.