የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጀግኖቻችን ላይ እያደረገ ያለውን ወከባ ሊያቆም ይገባል! እስረኞችን ማንገላታት ይቁም!
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጀግኖቻችን ላይ እያደረገ ያለውን ወከባ ሊያቆም ይገባል!
እስረኞችን ማንገላታት ይቁም!
አርብ ጥር 20/2008
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጀግኖች ታሳሪዎቻችንን አላግባብ እያንገላታ ይገኛል፡፡ በትናንትናው እለት በማረሚያ ቤቱ ከተነሳ ጸብ እና ወከባ ጋር በተያያዘ ‹‹እናንተ ናችሁ ያስበጠበጣችሁት›› በሚል መሪዎቻችን ላይ ተጽእኖ እያደረሰ ያለው የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ይህንን የሚደርግበት አንዳችም ማረጃ የሌለው ሲሆን ተነሳ የተባለው ብጥብጥም ቢሆን ከእነሱ ጋር አንዳችም የሚያያይዘው ግንኙነት አለመኖሩን ማጣራት ተችሏል፡፡ በብጥብጡ ወቅት ከታሳሪዎቻችን ብዙዎቹ ከደሴ ተከሳሾች ጋር በተያያዘ ለምስክርነት ተጠርተው ችሎት ላይ የነበሩ መሆናቸውን እያወቀ የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም ለማጥቃት እያኮበኮበ ያለው አስተዳደሩ ከማንም በላይ በተነሳው ብጥብጥ እጃቸው እንደሌለበት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ይልቁንም ካሁን በፊትም ቢሆን ባገኙት አጋጣሚ ጀግኖች ኮሚቴዎቻችንን ሲያዋክቡ እና ሲያስቸግሩ መቆየታቸው ለዓመታት ሲታይ የነበረ እውነታ ነው፡፡

መሪዎቻችን በእስር ባሳለፏቸው ዓመታት ሁሉ ከማእከላዊ ቶርቸር አንስቶ የተለያዩ ወከባዎች ሲደርሱባቸው ቆይተዋል፡፡ ቤተሰብ እንዳይጎበኛቸው እቀባ ማስቀመጥ፣ በጨለማ ክፍል ማሰር እና ጠያቂዎቻቸው ላይ የተለያየ እቀባ በማድረግ ማንገላታት ሁሉ ሞራላቸውን ለመስበር ጥቅም ላይ ሲውሉ የቆዩ መንግስታዊ ሴራዎች ናቸው፡፡ ግና ወኔያቸውን እና የሞራል የበላይነታቸውን ሊያሸንፍ የቻለ ሴራ እስካሁን አልታየም፡፡
በመሆኑም መንግስት የአገር ሀብት የሆኑ ብርቅዬ መሪዎቻችንን በሃት ክስ ማንገላታቱ ሳያንሰው በእስር ቤት ውስጥም ሰላማቸውን ለመንፈግ የሚደርገውን ጥረት አሳፋሪነት ተረድቶ በአስቸኳይ ወከባውን እንዲያቆም እናሳስባለን!
እስረኞችን ማንገላታት ይቁም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር