በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ተጠናክሮ ቀጥሏል።በዶዶላ ደህንነቶች ስልጤ የኦሮሞ ጠላት ነው የሚል ወረቀት መበተናቸው ታወቀ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ተጠናክሮ ቀጥሏል።በዶዶላ ደህንነቶች ስልጤ የኦሮሞ ጠላት ነው የሚል ወረቀት መበተናቸው ታወቀ:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Gambella‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Dodola‬

Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – በጉጂ በደብረጽጌ በገብረጉራቻ በሜታ በሜኢሶ እና ኣሰቦት የኦሮሞ ተማሪዎች አና የኣከባቢው ነዋሪዎች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚደረገውን ግድያ እና እስር በመቃወም ተቃውሞ ማሰማታቸው ታውቋል።በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን በዶዶላ ከተማ : የመንግስት ደህንነቶች ትናንት ለሊቱን በከተማው ውስጥ ስልጤ የኦሮሞ ጠላት ነው የሚል ወረቀት በትነው ማደራቸው ተሰማ ።በጋንቤላ ክልል በኣኝዋክ አና ኑዌር መካከል የተነሳው ግጭት የቀጠለ ሲሆን ኣስረኣንድ ሰዎች መገደላቸው ታውቃል::

Minilik Salsawi's photo.

በጉጂ ዞን በተደረገው ተቃውሞ የፖለቲካ እስረኞች አንዲፈቱ የተጠየቀ ሲሆን ህዝቡ ኣላሙዲን ከሻኪሶ ሳካሮ እና ኦኮቴ በማእድን ቁፋሮ የሚያገኘውን ጥቅም ለከተማዋ ታክስ አንዲከፍል አና የኣከባቢውን ተወላጆች ተጠቃሚ አንዲያደርግ በመጠየቅ ድምጻቸውን ያሰሙ ሲሆን ለክልሉ ይሁን ለኣከባቢው ጥቅም የማይሰጥ ከሆነ እንዲዘጋ ሲሉ ኣስጠንቅቀዋል።በሃረርጌ ክፍለሃገር የሚገኙ የኦሕዴድ ባለስልጣናት ከስልጣን መባረር አና ግድያ ኣንስቶ አስከ መታሰር አየደረሰባቸው መሆኑ ተጠቁሟል።የመኢሶ ኣስተዳዳሪዎች እና የኦሕዴድ ኣመራሮች ከስልጣናቸው የተባረሩ ሲሆን የጸጥታ ክፍል ምክትል ሃላፊው በወያኔ ኣግኣዚ ወታደሮች ሲገደል ሌላኛው በከባዱ ተደብድቦ ከቆሰለ በኋላ የደረሰበት ኣልታወቀም።የኣሰቦት ከተማ ከንቲባ ሕዝብ ፊት ከተደበደበ በኋላ ተይዞ የተወሰደበት ኣይታወቅም፤ የመኢሶ ወረዳ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ተባሮ በሌላ የኦሕዴድ ካድሬ ተተክቷል። ዛሬ ጠዋት ብደብረ ጽጌ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከኣርባ በላይ ተሰላፊዎች በኣግኣዚ ጦር ተይዘው ተወስደዋል።

ይህ በኢንዲህ አንዳለ በጋንቤላ ክልል በኣኝዋክ አና ኑዌር መካከል የተነሳው ግጭት የቀጠለ ሲሆን ኣስረኣንድ ሰዎች መገደላቸው ታውቃል፤ የወያኔ ኣገዛዝ ከፋፋይ ተጎሳ ፖለቲካ የጫረው ይህ ግጭት በካድሬዎች ከተጋጋለ በኋላ በዩንቨርስቲው ግቢ የተነሳ ግጭት ተስፋፍቶ የጋንቤላ ክልል ከተሞችን በማዳረስ ላይ ይገኛል።

በዶዶላ ደህንነቶች ስልጤ የኦሮሞ ጠላት ነው የሚል ወረቀት መበተናቸው ታወቀ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን በዶዶላ ከተማ የመንግስት ደህንነቶች ትናንት ለሊቱን በከተማው ውስጥ ስልጤ የኦሮሞ ጠላት ነው የሚል ወረቀት በትነው ማደራቸው ተሰማ ።በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውና ተፋፍሞ የቀጠለው የህዝብ አመፅ ያጨናነቀው የወያኔ መንግስት : እምነትን ከእምነት፣ አንድን ዘር ከአንድ ዘር በማጋጨት የህዝቡን ጥያቄ አቅጣጫ አስታለው ብሎ በማሰብ : የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ተንኮሎችን እየሸረበ መሆኑ ይታወቃል ።

የወያኔ መንግስት በዶዶላ የበተነው ወረቀትም የዚሁ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨትና እንዳይተማመኑ ለማድረግ በማለም የተሰራ ከንቱ ምኞት መሆኑን ለራዲዮ ዳንዲ ሃቃ ‪#‎RDH‬ የገለፁ አስተያየት ሰጪ : ይህ የመንግስት ተንኮል በእምነቱ በአስተሳሰቡ በአብዛኛው ማህበራዊ ህይወቱ የተቆራኘውን የስልጤ ህዝብና የኦሮሞ ህዝብ ሊያለያየው ቀርቶ የበለጠ እንደሚያቀራርበው ገልፀዋል ።በመላው የኦሮሚያ ክልል ውስጥ የስልጤ ተወላጆች እንደሚገኙ የገለፁት አስተያየት ሰጪ : የኦሮሞው ህዝብና የስልጤው ህዝብ ተዋውና ተከባብረው ከመኖር ውጪ : አንድም ቀን በመካከላቸው ችግር ተፈጥሮ እንደማያውቅ ገልፀዋል ።የስልጤ ህዝብ የኦሮሞ ህዝብ የጠየቀው ጥያቄ: የመብት ጥያቄ መሆኑን ተረድቶ ለጥያቄው አጋርነቱን አሳይቷል ያሉት እኚሁ አስተያየት ሰጪ : ወደፊትም የህዝቡ ጥያቄ እሰኪመለስ አጋርነቱ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል ።