በኣዋሳ የመሬት መንቀጥቀጡ ኣሰጋን ያሉ ተማሪዎች ላይ ተኩስ ተከፈተ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኣዋሳ የመሬት መንቀጥቀጡ ኣሰጋን ያሉ ተማሪዎች ላይ ተኩስ ተከፈተ።

የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲው እንዲዘጋ እና ወደየቤታቸው እንዲበተኑ ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበረ። ፌደራል ፓሊስ እንደተለመደው በዱላ እና ወደ ሰማይ በመተኮስ ሰልፉን ለመበተን የሞከረ ቢሆንም አልተሳካም። ሰልፉን ተከትሎም የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከመሸ ወደ ግቢው በመምጣት ትምህርት ለ፩፭ ቀን መዘጋቱን እና ተማሪዎች ወደየቤታቸው መሄድ እንደሚችሉ ገልፆላቸዋል።

መንግስት በሚዲያ በህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ቢልም ከትናንት በስቲያ ብሎክ ፴፮ በመሬት መንቀጥቀጡ ወቅት በተፈጠረ የኤሌክትሪክ መስመር ችግር በእሳት ሲያያዝ ህይወቷን ለማትረፍ ከ፫ኛ ፎቅ የዘለለች ተማሪ እንዲሁም የመሬት መንቀጥቀጡ በተከሰተ የመጀመሪያ ቀን የላይብረሪው ኮርኒስ ከወደቀባቸው እና በህክምና ይረዱ ከነበሩ ተማሪዎች መካከል የጋምቤላ ክልል ተወላጅ የሆነ ተማሪ መሞታቸውን ተማሪዎቹ ይናገራሉ።