ኢትዮጵያ “ነፃነት የሌለባት”፤ ኤርትራ “ከክፉዎች የከፋች” ተባሉ – VOA


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Ethiopian-federal-police attack-young-women
በዓለም ዙሪያ የሚሰማው የምጣኔ ኃብት ድቀት እና የማኅበራዊ ነውጥ ፍራቻ አምባገነን መንግሥታት በአውሮፓ አቆጣጠር ባለፈው 2015 ዓ.ም ይበልጥ አፋኝና ጨቋኝ እንዲሆኑ ሰበብ ሳይሰጣቸው እንዳልቀረ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ሁኔታ ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ፍሪደም ሃውስ የሚባለው ነፃ ቡድን በዚህ ሪፖርቱ የሃገሮችን የዴሞክራሲያዊ የነፃነት ይዞታዎች ገምግሞ በደረጃ አስቀምጧቸዋል፡፡ አምባገነን አገዛዞች ባለፈው የአውሮፓ ዓመት በ2015 ዓ.ም ይበልጥ የከፉ መሆናቸውን ይህ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ይዞታ ሪፖርት ይናገራል፡፡

መንግሥታቱ የሚጠቀሙባቸው እጅግ የከፉ የአፈና ዘዴዎች፣ የሽብር ፈጠራ ጥቃቶች መብዛት እና የምጣኔ ኃብት መላሸቅ፣ ነፃነት በዓለም ዙሪያ እየተጉላላች፣ ይዞታዋ ወደ አስፈሪ ሁኔታ እያዘገመ መምጣቱ እያሰጋ መሆኑን ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡

ተቀማጭነቱ ዋሺንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው ፍሪደም ሃውስ የሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ተሟጋች ቡድን ባለፈው የአውሮፓ 2015 ዓ.ም የዓለም የነፃነት ይዞታ ለአሥረኛ ተከታታይ ዓመት እያሽቆለቆለ የመጣበት ዓመት እንደነበረ አስታውቋል… ያዳምጡ → listen