ሰራዊቱ ለውጊያ የሚሆን ሞራል የለውም ሲል የሕወሓት ወታደራዊ ሹማምንት ስብሰባ ጠቆመ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በሃገሪቱ መጭውን ጊዜ ኣስመልክቶ የሕወሓት ወታደራዊ ባለስልጣናት ስብሰባ በመቀመጥ የተወያዩ ቢሆንም በሰራዊቱ ላይ ያለውን መተማመን አጅግ የወደቀ አና ለውጊያ ሞራል የለውም የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሳቸው ታውቃል።
ከዚህ ቀደም እንደተባለው የትግራይ ሚሊሻዎችን በወታደራዊ መልኩ ማደራጀት የትግራይ ወጣት በውጪ እና በውስጥ የሚገኘውን የሕወሓት ደጋፊ ቢሆንም ባይሆንም ኣስፈላጊውን ስልጠና አና ትብብር በማድረግ በጥቅም በትምሕርት እና ሌሎች ድጎማዎች በመተባበር ማስታጠቅ።የደህንነት ሰራተኞች በትግራይ ተወላጆችና በለላው የኢትዮጵያ ክፍል ተወላጆች መካከል ክፍተት ለመፍጠር የተጀመሩ የሚሰሩ ስራዎች እንዲጠናከሩ ማድረግ ለዚህም የተቃዋሚዎች ጥንካሬ በስሜታዊነት ላይ ስለሚያደላ የፖለቲካ ጥላቻው ስለሚባባስ ይህንን ተገን ኣድርጎ የትግራይ ወጣቶችን መቆጣጠር ይህ ካልተደረገ ሰራዊቱ የውጊያ ሞራል ስላሌለው ነገ ችግር ቢመጣ ወደ ሕወሓት ኣዙሮ እንደሚተኩስ የታወቀ ስለሆነ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ኣፋጣኝ ስራዎች እንዲሰሩ ወስነዋል፥
ከዚህ ጋር በተያያዘ ተቃዋሚዎች የሕዝብ ኣመጽ በገፋ ሰኣት ላይ ምናልባት መንግስት ቢናጋ ድንገት ስልጣን እንዳይዙ ሃገር በማረጋጋት ስም ለመፈንቅለ መንግስት የሚሆን ቡድን ከደህንነቱ አና ወታደራዊ ክፍል ተመልምሎ በከፍተኛ ምስጢር እንዲዘጋጅ እና ችግር በተፈጠረ ሰኣት ስታንድ ባይ የሆኑና የሕወሓት ባለስልጣናትን የሚያሸሽ ስራ የሚሰሩ ተግባራት እንዲከናወኑ ስለማድረግ በውይይቱ ወቅት ተነስቶ ለፕሮፖዛል ነደፋ ጉዳዩን አንዲይዙ ለተደረጉ የደህንነትና ወታደራዊ ሹማምንት ተላልፏል።በዚህ ኣጋጣሚ ከሕወሓት መስሪ ድርጊት የምንማረው እና የምንረዳ ነገር ስላለ የለውጥ ሃይሎች እጅግ በጣም በተጠንቀቅ ይህንን እኩይ ሴራ በማክሸፍ አና በጋራ በመተባበር በክፋት ላይ ተመስርቶ ስልጣኑን ለማስረዘም እና ዘርፎ ለመጥፋት የሚያልመውን የማፊያ ቡድን ከነኣባላቱ መደምሰስ ግዴታ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ