በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በሌሎች ወገኖቻቸው መካከል ለማንደድ የሚሞክረውን እሳት በጋራ የማጥፋት ጥሪ!
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
#Ethiopia #ShareEthioHarmony #EBCDocumentary #1460DaysOfPeacefulStruggle #EthioMuslims #MinilikSalsawi
‹‹ማህበራዊ መስተጋብራችንን እንካፈል!››
መንግስት በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በሌሎች ወገኖቻቸው መካከል ለማ
ንደድ የሚሞክረውን እሳት በጋራ የማጥፋት ጥሪ!
ከረቡእ ጥር 18 እስከ እሁድ ጥር 22/2008 የሚቆይ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ
ረቡእ ጥር 18/2008
መንግስት በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በሌላ ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻቸው መካከል እሳት ለመለኮስ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ካሁን ቀደም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በደህንነቶቹ የሚፈጽማቸውን ስውር ጥቃቶች ተገን በማድረግ የመቃቃር ስሜት ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን የእምነት ቦታዎች ላይ ጥቃት በማድረስም ሴራ ለመጎንጎን ሞክሯል፡፡ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ ደግሞ በሊባኖስ በእምነቶች መካከል ቀውስ በማስከተል የሚታወቀውን ‹‹አህባሽ›› የተባለ አንጃ በማምጣት ህዝበ ሙስሊሙን በግድ ለመጋት ሲሞክር ቆይቷል፡፡ ይህም አልሳካ በማለቱ እና ህዝበ ሙስሊሙ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን በጽናት በመቀጠሉ የተለያዩ ‹‹ጥናታዊ›› ፊልሞችን በመስራት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለአገሪቱ ስጋት እንደሆኑ ለማሳየት ሞክሯል፡፡ አልሐምዱሊላህ መላው ኢትዮጵያውያን ይህንን እኩይ ፕሮፓጋንዳ ጆሮ በመንፈግ ለዘመናት የኖረ መልካም የህዝብ ለህዝብ መስተጋብራችን በማይረባ ሴራ እንደማይናድ በተግባር አስመስክረዋል፡፡
ከሰሞኑ መንግስት በኢቲቪ ያቀረበው ‹‹የማንቂያ ደወል›› የተሰኘ ‹‹ጥናታዊ›› ፊልምም ቢሆን የዚሁ የመንግስት ክብሪት የመጫር ሙከራ አንዱ አካል መሆኑን ካሁን ቀደም የገለጽን ሲሆን ይህን እኩይ የመንግስት ሴራ ለማክሸፍ ሁላችንም መተጋገዝ እንደሚገባን ማስታወሳችንም አይዘነጋም፡፡ ይህንን የማድረጉ ሃላፊነት ደግሞ በመላው አገሩን በሚወድ ኢትዮጵያዊ ጫንቃ ላይ የወደቀ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ሳምንት ከምናደርጋቸው ሌሎች እንቅስቃሴዎች ጎን ለጎን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር የምንኗኗርባቸውን መልካም ማህበራዊ መሰረቶች እና ድንቅ መስተጋብሮች በማህበራዊ ሚዲያ የምንካፈልበት (ሼር የምንደራረግበት) አነስተኛ መርሃ ግብር ይኖረናል፡፡
ከዛሬ ረቡእ ጥር 18 ጀምሮ እስከ እሁድ ጥር 22/2008 በሚቆየው በዚሁ ዘመቻችን በእለት ተእለት ኑሯችን በጎረቤታችን፣ በሰፈራችን እና በስራ ቦታችን ከሚገኙ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወንድም እና እህቶቻችን ጋር ያለንን መልካም ቅርርብ እና መተሳሰብ የሚያሳዩ ገጠመኞቻችንን፣ አኗኗራችንን እና ትብብራችንን በቻልነው ያክል በጽሁፍ (ወይም በሌላ አመቺ በሆነ መንገድ ሁሉ) በማስፈር #ShareEthioHarmony የሚለውን ሐሽታግ በመጠቀም በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶቻችን ሼር እናደርጋለን፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሃይማኖታዊ ማንነታችንን ሳንለቅ እና እሴቶቻችንን ሳናፈርስ ከሌሎች ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ጋር መልካም ጉርብትና እና ወዳጅነት መስርተን የምንኖር መሆኑን፣ ይህም በመንግስት እኩይ ሴራ ሊናድ የማይችል መለያ ባህሪያችን መሆኑን በተግባር እናስመሰክራለን፡፡ ‹‹ሙስሊሞች መጡልህ!›› እያለ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ወገኖቻችንን ሊያስፈራራ የሚሞክረውን መንግስታዊ ሴራ እና የዶኩመንታሪ ፊልም ጋጋታ የማንቀበለው መሆኑን በተግባር እናሳያለን፡፡ ሌሎች ወገኖቻችንም ትስስራችንን እና መስተጋብራችንን በምንካፈልበት በዚህ ታላቅ ሳምንታዊ ድግስ በመሳተፍ ድምቀት ያለውን መልካም ጉርብትናችንን ለዓለም እናሳይ ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናደርጋለን፡፡
አዎን! የመንግስት እኩይ ሴራዎች በየጊዜው ሊጭሩ የሚሞክሩትን አገር አጥፊ ሰደድ እሳት እንደወንዝ በሚፈስሰው መልካም ጉርብትናችን እና ወገናዊ ትስስራችን ለማጥፋት ጊዜው አሁን ነው! ወደጥርጣሬ እና በዓይነ ቁራኛ ወደመተያየት በመግፋት ርካሽ ፖለቲካዊ ጥቅም ለማትረፍ የከጀለውን መንግስት አሳፍሮ መመለስ የሚኖርብን ዛሬ ነው! እኛ ኢትዮጵያውያን መካከላችን ለመግባት ለሚፈልጉ እኩያን ቀዳዳ የማያስከፍት መልካም አኗኗር እና ወገናዊ ህብር እንዳለን የምናስመሰክረው ዛሬ ነው! በዚህ ሳምንት መልካም ጉርብትናችንን ለዓለም ይፋ እናደርጋለን…. እጃችሁ ከምን???
‹‹ማህበራዊ መስተጋብራችንን እንካፈል!››
‹‹ትግላችን አብሮነትን የሚያጎለብት፣ የውድ አገራችንን ሰላም እና ደህንነት ታሳቢ ያደረገ ነው!››
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!
Like ☑ Comment ☑ Share ☑
