የታምራት “ጥፊ”


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Woldeselassie Woldemichael
የአቶ ታምራት ላይኔና ስዬ የክስ ሂደት ሲታይ እኔና ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ችሎት እየተገኘን እንከታተል ነበር። አንድ ጊዜ ችሎት ከመጀመሩ በፊት ታምራት አቤቱታ አለኝ አሉ። ሲናገሩም፥ “ከትላንት በስቲያ እዚህ ፍ/ቤት ውዬ ስሄድ የወህኒ ቤቱ አዛዥ ቢሮ አስጠሩኝና የመለስን ስም ለምን ታነሳለህ ብለው በጥፊ መቱኝ። ነገም ሊገድሉኝ ይችላሉ…” አሉ። በሚቀጥለው ቀጠሮ አዛዡ ቀረቡ። ሲጠየቁ – “ጠርቼ አናገርኳቸው እንጂ አልመታኋቸው” አሉ። በግርምት ያደመጡት ታምራት – “የጠራኝ ፖሊስ ውጭ እንዲሆን ነግረውት (ምስክር እንዳይሆን) ነው የመቱኝ። አልመታሁትም ካሉ ለህሊናዎ እተወዋለሁ! ..እኔ በአንድ ወቅት ትልቅ ስልጣን ነበረኝ። ዛሬ በጓደኞቼ ተገፍቼና ጨለማ ውስጥ ተጥዬ በእርሶ በጥፊ ለመመታትና እግርዎ ስር ለመውደቅ በቃሁ። መለስ ነው ይህን የሚያደርገው። የጊዜ ጉዳይ ነው። አንድ ቀን እኔ ያለሁበት ይገቡ ይሆናል!” አሉ በሀዘን ስሜት። ዋናው ተዋናይ የደህንነት ሹም ወ/ስላሴ በስርቆት (የስልጣን ሽኩቻ?) ወህኒ ከወረደ 3 አመት ሊሆን ነው። ዛሬም ንፁሀንን የምትገድሉ፣ ንፁሀንን የምታስሩና የምታሰቃዩ እንዲሁም ትእዛዝ የምትሰጡ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ከመጠየቅ አትድኑም!