የቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም የሚያቀናብርለት የ3 ግራሚ ተሸላሚ የሆነው ዝነኛው አሜሪካዊ አቀናባሪ ጎርደን ዊሊያምስ ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አዲስ መረጃ የቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም በተመለከተ:-

የመጨረሻውን አልበም ካወጣ አራት አመት የሆነው ዝነኛው ቴዲ አፍሮ ቀጣዩን አልበም ኒዮርክ ስትዲዮ ለመስራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታወቀ። ቴዲ ከአዲሱ አልበም ውስጥ አምስት ዘፈኖቹን የሚያቀናብርለት ታዋቂውና የሶስት ግራሚ ተሸላሚ የሆነው ዝነኛው አሜሪካዊ አቀናባሪ ጎርደን ዊሊያምስ ነው።አዲስ አበባ ላይ የተጀመሩትን ስራዎቹን ይዞ ወደ ኒዮርክ ያመራው ቴዲ አፍሮ ዘፈኖቹ በጎርደን ስቲዲዮ እንዲቀናበሩለት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።በአሁኑ ወቅት ለመድረክ ስራ ካሊፎርኒያ የሚገኘው ቴዲ ስራውን ሲጨርስ ወደ ኒዮርክ በመመለስ እዛው ባለው ግዙፍ ስቲዲዮ ስራውን እንደሚሰራ ታውቃል።ዝነኛው አቀናባሪ ጎርደን ዊልያምስ ከዚህ በፊት ለአሊሺያ ኪስ: ሎሬን ሂል: ካርሎስ ሳንታና: አሚ ዋይንሀውስ እና ለፊፍቲ ሴንት ምርጥ ስራዎችን የሰራና ሶስት የግራሚ ሽልማቶችን ያገኘ ትልቅ የሙዚቃ ሰው ነው።በተያያዘ ዜና ቴዲ በአዲሱ አልበሙ ከቦብ ማርሌ ልጅ ዳይመን ማርሊ ጋር በጋራ የሚጫወቱት የሬጌ ስራ እንዳለውም ለማወቅ ተችላል።