ሕወሓት በፈጠራና በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም በጎሳ ፖለቲካ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ሕወሓት በፈጠራና በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም በጎሳ ፖለቲካ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው። #Ethiopia #Oromoprotests #EPRDF #MinilikSalsawi #Ethiopianism
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ንቅናቄ ተከትሎ የሚራገቡ የዘረኝነት ኣጀንዳዎች እየበረቱ ነው፤በስሜት የሚነዱ ጥቂቶች ፣የሕወሓትን መሰረታዊ የዘረኝነት ኣጀንዳ የሚያራግቡ ጥቂቶች፣ ታሪክ ቀመስ ምሁር ነን ባዮች የኣንድ ብሄር የበላይነት የሚያጦዙ ሹምባሾች፣በዕልህ የገቡበት ሃገር ወዳድ የዋሃን፣አንዲሁም በኦሮሞ ሕዝብ ደም ላይ ቆመው በኣንድነት ስም ተሸፍነው ሕዝብ ለሕዝብ ለማባላት ሃገር ለመበጣጠስ ያሰፈሰፉ ኣስመሳይ የፖለቲካ ሴራ ተብታቢዎች ፣በተንኮል ገብተው በተንኮል ወጥተው በተንኮል አየኖሩ ያሉ በኦሮሞ ስም የሚነግዱ የሃገር ቤት ቅጥረኞች አና የዲያስፖራ ነጭለባሽ ኣጭበርባሪዎች ዘረኝነትን በማራገብ ሃገሪቱ ለሕዝባዊ ለውጥ የምታደርገውን እመርታ ኣደናቅፈው በሕወሓት ኣምባገነን ጉያ እንደተወሸቀች እንድትኖር በጭፍን እየተራወጡ ይገኛሉ።
ይህን ሰሞን እያየን ያለነው ጉዳይ አጅግ የሚገርም እና የለውጥ ሃይል ነን የሚሉ ኣማሳኞች ሳይቀሩ አየተራወጡ ያሉበት የዘረኝነት መነባነብ በኣገሪቱ ስር አንዳይሰድ ትውልዱ እንዳይበከል የሚያስፈራ ጉዳይ መሆኑ ውሎ ኣድርዋል፥፥የሚደርሱኝ መረጃዎች አንደሚጠቁሙት ዘረኝነትን ለማስፋፋት የተለያዩ ኣካላት ገንዘብ መድበው በሃገር ቤት ያለውን ወጣት ለፍጅት እና ለኣጀንዳቸው ማስፈጸሚያ አያጩት ነው።ይህ ደግሞ የሕወሓት አጅ የለበትም ማለት ዘበት ነው። ሕወሓት ወንጀለኘ አና ኣሸባሪ ዘረኛ እና ኣስመሳይ ማፊያ እና ዘራፊ ሕገወጥ ድርጅት ነው።
በዲያስፖራው ዘንድ በስፋት አየተራገበ ያለው ይህ ወያኔ ወለድ በሽታ ዋናው ክስተቱ የገዢው ፓርቲ ሕወሓት የፈጠረበት የበታችነት ስሜት ሲሆን በሕወሓቶች ዘንድ ከበታችነት ለመላቀቅ በሚደረግ መራወጥ የሚፈጠር ጥላቻ ዘረኝነት የሰረጸባቸው ያዩት የሰሙት ሁሉ የሚያስደነብራቸው የበታች መደቦች ኣንድ ጉዳይ በተነሳ ሰኣት ሁሉ ዘር ላይ የሚንጠለጠሉ እና የስልጣን ጥማትን ለማርካት ሲባል የሃገር አና ሕዝብን ሃብት ለመበዝበዝ የነገ ትውልድ ኣደጋ የማይታያቸው ሕዝብን በዘር በመከፋፈል ለመግዛት የሚያደርጉት ደባ ነው። ቆቤ ኦሮሞ ፤ ቤተ ኣማራ ፤ ትግራዋይ ምናምን እየተባለ በወያኔ የደህንነት ተቍማት ስራ የሚደራጁ ክንፎች በነማን እንደሚመሩ በነማን በጀት እንደሚጦዙ የኣጀንዳዎቹ መነሻዎች እነማን እንደሆኑ ምስክር ኣያስፈልግም።
ይህ ወያኔ ወለድ የሆነ የዘረኝነት በሽታ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ያህል ባይስፋፋም በዲያስፖራው ዘንድ ግን ስር የሰደደ በሽታ ከሆነ ሰነባብዋል።ጥቂት ዲያስፖራዎች በሃገር ቤት ያሉትን ወጣቶች በገንዘብ በመግዛት ዘረኝነትን ለማስፋፍት ሲጣጣሩ ይስተዋላል።ኣለም በኣንድ የእድገት መሰረት ላይ ለመመስረት በቴክኖሎጂ እና ትልልቅ ግኝቶች ላይ ባተኮረበት በዚህ ዘመን ጥቂቶች የሚፈጥሩት የድህረገጽ የዘረኝነት ወከባ አጅግ ኣሳዛኝ እና ኣስደንጋኝ ነው።ሕወሓት አነዚህን በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም ኢትዮጵያውያንን በዘር ከፋፍሎ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው።በዲያስፖራው ጉያ ስር ተወኅቀው የወያኔን የዘረኝነት ኣጀንዳ ለመፈጸው አያወቁም ሳያውቁ ደፋ ቀና የሚሉ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ሊያስቡ ይገባቸዋል።የማያዘልቅ ጸሎት ለቅጽፈት መሆኑን ተረድተው ከዘረኝነት በሽታ ሊላቀቁ ይገባቸዋል። በጥቅም ላይ የተመሰረተ ወጣቱ ያላመነበት የዘረኝነት መስፋፋት ውጤቱ በእኩይ ተግባር ላይ ለተሰማሩ ዘረኞች ኣደጋ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ