ሰማያዊ ፓርቲዎች የሕዝብን ትግል መምራት ሲገባቸው በውስጥ የፓርቲ ሽኩቻ ተጠምደዋል። (ብር ኣምባር)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


@semayawiParty #Ethiopia ሰማያዊ ፓርቲዎች የሕዝብን ትግል መምራት ሲገባቸው በውስጥ የፓርቲ ሽኩቻ ተጠምደዋል። (ብር ኣምባር)
በኦሮሚያ ክልል በሕዝብ ተነሳሽነት በተለያዩ ኣከባቢዎች የሕወሓት መራሹን ኣገዛዝ በመቃወም ታላላቅ የሕዝብ እምቢተኝነቶች አና ተቃውሞዎች እየተካሄዱ ይገኛል።እንዲሁም በጎንደር ኣከባቢ ከፍተኛ የሕዝብ ተነሳሽነት ለለውጥ እና የኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለል ተቃውሞ ይታያል።በሃግሪቱ ዙሪያ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ሕዝብ ለለውጥ ያለውን ፍላጎት ከማሳየቱም በላይ የኣስተባባሪ የኣደራጅ የመሪ ያለህ የሚል ትግል አያጧጧፈ ይገኛል።
ይህ አንዲህ ሆኖ ሳለ በሃገር ቤት የሚካሄደውን የሕዝብ ትግል የሚያስተባብር ሃይል ድርጅት ያለህ የመሪ ያለህ በሚባልበት በዚህ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ በውስጥ ሽኩቻ አየታመሰ እንኳን የሕዝብ ትግል ሊመራ ይቅርና እርስ በእርሱ እየተናከሰ ይገኛል።ከድርጅቱ ስራ ኣስፈጻሚ እስከ ዲሲፒሊን ኮሚቴ ከሕግ ክፍሉ እስከ ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ወዘተ በድርጅቱ ውስጥ እርስ በእርስ በመኮራኮም ድርጅቱን ለኣደጋ \ለምርጫ ቦርድ መንጋጋ ኣባላቱን ለሕወሓት የሃሰት ክሶች ድጋፍ የሕዝብን ትግል ደሞ ተኣማኒነት እንዳይኖር ለማቀዝቀዝ የሚደረገው ጉዞ ለወደፊቱ ተስፈኛ የለውጥ ፈላጊ ትውልድ ተስፋ ከማጨለም ተለይቶ ኣይታይም።

በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም አና ዲሞክራሲ የሰው ልጅ መብት እንዲከበር ለለውጥ የታሰሩ የደሙ እና የሞቱ የሰማያዊ ፓርቲ ኣባላትን ማሰብ ያስፈልጋል።ሰማያዊ ፓርቲ በወጣቶች አስከተገነባ ድረስ በሕዝባዊ ተቃውሞ መሪነት ትውልዱ ቢፈልገውም ይባስ ብሎ ኣባላቱን በመወንጀል ስራ ኣስፈጻሚውም ነገር በማቀጣጠር ጡዘት ውስጥ ስለተለቁ ከወረቀት ላይ ነብርነት\መግለጫ ኣልዘለሉም።የፓርቲውን ጥቅም ለገዢው ፓርቲ ኣጋር ሚዲያዎች ኣሳልፎ አስከመስጠት የሚያሳየው ነገር በድርጅቱ ውስጥ ኣለመተማመን እና የፖለቲካ ሾኬ መኖሩን ነው።ስለዚህ ኣባላቱ በኣፋጣኝ ሽኩቻ አና ጠለፋ ሾኬ አና ኣሉባልታቸው ኣቁመው ፊታቸውን ወደ ሕዝብ ትግል በመመለስ ትግሉን የመምራት ግዴታ ኣለባቸው።