ድግሥ በቤተ-መንግሥት = ይድነቃቸው ከበደ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ድግሥ በቤተ-መንግሥት

‪#‎በአዲስ_ገጽ_መጽሔት‬ በባለፈው ሳምንት ለንባብ የበቃ

“በኢሉባቡር መቱ በመንግሥት ቅጥረኞች ሙሽራ ይገደላል፤በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በቤተ-መንግሥት ደግሞ የአቶ ኃይለማርያም ልጅ ዶ/ር ሶስና እና ከእጮኛዋ አቶ አቤል ድል ባለ ድግስ ይጋባሉ”
————————————-

እንደ መንደርደሪያ ፣ በስታዲዮም አካባቢ የሚነገር አንድ የአራዳ ልጆች ቀልድ አለ(አሁን አሁን ላይ በስፋት ይነገራል ፤የ“ወላይታ ዲቻ” የእግር ኳስ ቡድን ተጫዎቾች ተጋጣሚያቸውን አሸንፈው ዋንጫ ይረከባሉ፣የያዙትን ዋንጫ ይዘው ወደ-ቤተመንግሥት እየጨፈሩ ይሄዳሉ ፣የቤተ-መንግሥቱ ጠባቂ “ምንድነው…..ምንስ ፈልጋችሁ መጣችሁ?” በማላት ይጠይቃል ፣ይሄን ጊዜ ተጫዋቾቹ “ አሸንፈን የተረከብነው ዋንጫ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለማሳየት ነው”ይላሉ፡፡ጠባቂው ይሄን ጊዜ “አንዴ ጠብቁ” በማላት ፣ወደ-ውስጥ በመግባት ለቤተ-መንግሥቱ አዛዥ “ጌታዬ ከበር ላይ የወላታ ዲቻ ተጫዋቾች አሸንፈን ይዘን የመጣነውን ዋንጫ ለኃይለማርያም ማሳየት እንፈልጋለን ይላሉ ምን ይሻላል?” በማላት ለዋና ሰውዬ ይጠይቃል፣ ዋናው ሰውዬ በስጨት ብሎ “ ተመለሱ በላቸው፣የገባውም አለወጣም ብሏል እንኳን ሌላው ሊገባ” አላቸው ይባላል፡፡

አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ እድለኛ አይደሉም !በእሳቸው እና በሚወክሉት መንግሥታቸው የሥልጣን ዘመን፣ አገራችን ኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ ፤የመንግሥት የአስተዳደር ብሉሹነት እና ሽባነት በታየበት፣የዴሞክራሲ እጦት፣ራሃብ፣ስደት፣ጦርነት እና አለመረጋጋት ባለበት ሁኔታ ፤ሴት ልጃቸው ዶ/ር ሶስና እጮኛዋ አቶ አቤል አየለን በቤተ-መንግሥት ለመዳር በቅተዋል፡፡ ልጃቸውን ዳሩ መባሉን ይባሉ ፤ ግን አንድ የኢትዮጵያ መሪ ልጃቸውን ዳሩ ለመባል በሰዉ ሰውኛ የሚለካ በቂ የህሊና ልዕልናን እና የበላይነትን (ፈረሃ እግዚአብሔርንም ይጨምራል) ይጠይቃል፡፡

የአባት እዳ ለልጅ ሆነና ነገሩ ፣ይኸው ልጅ በወላጅ ወንጀልና ግፍ፣ ዘመኗን ሙሉ የምትኮራበት ሣይሆን ፤የምትሸማቀቅበት የሰው ሰውኛ ደስታዋን በአደባባይ ሣይሆን በጓዳ የምትገልፅበት ፣በታሪክ ማህደር የዛ የአምባገነኑ ሥርዓት መንግሥት መሪ ልጅ፣ ድግስ እና “እሷ” ከማላተ የማያልፍ፣ከድሃ ተስካር የማይበልጥ ይሄን ከማላት ፈቀቅ የማይል ፣ ጋብቻና ድግስ፡፡አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በእሳቸው ፍቃድ ሣይሆን በእነሱ ፍቃድ በቤተ-መንግሥት ለማየት ችለዋል፡፡

አልፎ አልፎ ካልሆ በቀር ዘወትር በታሪካ ውስጥ የማይከሰተው የቤተ-መንግሥት የሠርግ ድግስ ፤በኢትዮጵያ ታሪክ ይሄኛው ከአርባ ዘጠኝ ወይም ከግማሽ ምእት ዓመት በኋላ የተከሰተ አጋጣሚ ነው፡፡ይህ አጋጣሚ የባለፉትን ለማስታወስ እንዲሁም መጪውን ለመቆጠር የሚኖረው የማስታወስ አገልግሎት እንደተጠበቅ ይሆናል፡፡ይህም አገልግሎት መስጠቱ በራሱ ዋጋ አለው ከተባለ ዋጋውን እነሱ ቢወስዱት ምንም አይደለም፡፡

አቶ ኃይለማርያም በልጆቸው የሠረግ ድግስ ፣ከመሰሎቻቸው ጋር ደስታ-በደስታ ቢሆኑም፣ የመምሀር ፍፁም አባተ ቤተሰቦች ግን፣ በቤታቸው ሐዘን ገብቷል፡፡የሆነው ነገር እንዲህ ነው ፣በኢሉባቦር መቱ ወረዳ ቅዳሜ ታሕሳስ 30 ቀን 2008 ዓ.ም፣ መምህር ፍፁም አባተ ከፍቅረኛው ፍሬህይወት በለጠ ጋር የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት ለመፈጸም፣ ወዳጅ ዘመድ ተሰብስቦ እንደ-ሀገራችን ወግና በአል ዋዜማውን በሚያሰልፉበት ወቅት፣የመንግሥት ታጣቂ የሆኑ የፌዴራል ፖሊሶች ከልካይ በሌለበት ጫጉላ/ሙሸራ መምህር ፍፁምን በጥይት ደብድበው ገድለውታል፡፡ይህ ዜና በማህበራዊ ድረ-ገጾች በሰፊው ተሳርጭቶ ይገኛል፡፡ የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት አሰመልክቶ የክልሉ እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ እስካሁን በይፋ የሰጡት ማስተባባይ ሆነ ምላሽ ምንም የለም፡፡

የደስታ ጊዚያቸው ወደ-ሐዘን የተቀየረባቸው የመምህር ፍፁም አባተ ቤተሰቦች ለእኔ የብዙ ነገር መገለጫዎች ናቸው፡፡በኢሉባቡር መቱ ወረዳ በምንግሥት ኃይሎች ሙሽራ ይገደላል፤በቤተ-መንግሥት ደግሞ ድል ያለ ሠርግ ይደገሳል፡፡ሙሹሮችም ነሕዝብ ሃብት በመንግሥት ወታደሮች፣በልዩ ጥበቃ ታጅበው የደስታ ጊዚያቸውን አሳልፈዋል፡፡የሚበላው ምግብና መጠጥ ግን የመምህር ፍፁም አባተ የግፍ ደም ሆነ ለእኔ ይታየኛል፡፡

የቤተ-መንግሥት የሠርግ ድግስ ሲወሳ በዋነኝነት፣ ከዛሬ አርባ ዘጠኝ ዓመት በፊት እንጂ እስከአሁን ምንም ዓይነት የሠርግ ድግስ አልተደገሰም፡፡በ1959 የዚያን ጊዜ የጎንደር ክፍለ ሃገር ጠቅላይ ገዢ የነበሩት፣ ጀኔራል ነጋ ተገኝ ልጅ ልእልት ሂሩት በሚያገቡበት ወቅት በቤተ-መንግሥት ድል ያለ ድግስ ተደግሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ከ1959 ወደ-ኋላ ባሉት ጊዜያት በተለያየ ወቅት የሠረግ ሥነ-ሥርዓቶች በላይኛው እና በታችኛው ቤተ-መንግሥት ተካሂዶአል ፡፡ያሁኑን ድግስ ልዩ የሚያደርገው ነገር ይህች ምስኪን ሀገር ያለችበትን ሁኔታ ያየን እንደሆነ ነው፡፡ከዚህ ጋር የተያያዙ ሁለት ዋና ዋና መመሳሰሎችን በቀደሙ መንግስታት እናስታውሳለን!በንጉሡ ዘመን በሚሊየን የሚቆሩ ኢትዮጵያዊያን በረሃብ እየረገፈ ባለበት ወቅት የተደገሰውን የዉሻቸውን ልደት፤…….በደርጉ ዘመን ተመሳሳይ ድርቅ ሚሊየኖችን እያረገፈ የተደገሰው የአስረኛው አመት የመንግስቱ ፊሽታ (የኢሕዲሪ ምስረታ)፡፡ከዚህ አንጻር ሳየው ነው የኃይለማርያምን ድግስ አሳዛኝነትም አሳፋሪነትም የምንረዳው፡፡

ታሪኩ ደሳለኝ(የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም) ይህን ጉዳይ በተመጠኑ ቃላት እንደሚከተለው በማኅበራዊ ድረ ገፅ ላይ የጻፈውን በማስነበብ ጽሑፌን ልቋጭ፡፡ “ከመንገዱ ማዶ አንዲት እናት አለች-ፀጉሯን ተተኩሳ በፈገግታ ደምቃ በልጇ ሠርግ ላይ ምን ጎደሎ ይሆን ብላ በሀሳብ የተያዘች፤ከመንገዱ ማዶ አንዲት እናት አለች በጠይም ፊቷ ላይ ሐዘን ተደርቦ በልጇ ሞት ምክንያት አንጀቷ ያረረ እህህ በማለት አንገቷን የደፋች፤ከመንገዱ ማዶ አንዲት እናት አለች በሰርገኛው ጨኹት ራሷን ረስታ ጎንበስ ቀና ብላ እያስተናገደች በልጇ ወግ ማዕረግ እጅግ ተደስታ ፍድቅድቅ የምትል፤ከመንገዱ ማዶ አንዲት እናት አለች መቀነቷን አስራ ነጠላ አዘቅዝቃ እንባ እያናወዛት ደረቷን በመምታት በልጇ ሞት ምክንያት ራሷን የረሳች፡፡…….እነዚህ ሁለት ሚስቶች/እናቶች በአንድ አገር የሚኖሩ በግብርም በስምም የማይገናኙ ሁለት ባል አሏቸው፤አንደኛው ሚኒስትር አንደኛው ገበሬ አንኛው አሰገዳይ አንደኛው ቀባሪ፡፡”
ይድነቃቸው ከበደ

Yidnekachew Kebede's photo.