በባሌ ክፍለሃገር የሕወሓት ባለሃብቶች ንብረት ወደመ።ለጥምቀት በኣል የወጡ የኦሮሞ ወጣቶች ከኣዲስ ኣበባ ታፈሰው ታሰሩ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኦሮሚያ ባሌ ክፍለሃገር ውስጥ ጣዕመ ወልደየስ እና ቤተሰቦቹ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ንብረት የሆነው የእርሻ ማሳ በእሳት ቃጠሎ ወድሟል ። ለጥምቀት በኣል የወጡ የኦሮሞ ወጣቶች ለተቃውሞ የሚያነሳሱ ዜማዎችን ኣዜማቹሃል በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ ከኣዲስ ኣበባ ከተለያዩ ኣከባቢዎች ታፈሰው መታሰራቸው ታውቋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቡራዩ ኣከባቢ የሚገኙ ወጣቶች ተቃውሞ ሲያሰሙ መዋላቸው ተጠቁሟል።በጥምቀት በዓል ወጣቶች ተደብድበዋል፥፥በኣምቦ የወያኔ ወታደሮች ከተማውን በመውረር ሕዝቡ በዓሉን አንዳያከብር እንቅፋት ሲፈጥሩ ተስተውሏል።
በሃረር ከተማ ተቃውሞ ተካሂዷል።በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች የጥምቀት በዓልን ተከትሎ ተቃውሞዎች ሲሰሙ መዋላቸው ታውቋል።