ከጋምቤላ እስከ ኤርትራ በጥይት ከመቁሰል እስከ አድካሚ የበረሃ ጉዞ አስደናቂ የወጣቱ ተጋድሎ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኢትዮጵያ ምድር የደም ጎርፍ ተራራዉን ተሻግሮ ፈሰሰ።

Enat Alem Ethiopia's photo.

ከጋምቤላ እስከ ኤርትራ በጥይት ከመቁሰል እስከ አድካሚ የበረሃ ጉዞ አስደናቂ የወጣቱ ተጋድሎ።
ይህ ሁሉ የሆነዉ ፓለቲከኛ ጋዜጠኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ስለሆነ አይደለም። የሰራዉ ወንጀል የለም። የሆነዉ ሁሉ የሆነዉ አማራ ስለሆነ ብቻ ነዉ።
2006 አ.ም መጨረሻ ጀምሮ በምእራብ ኢትዮጵያ አማራ በተባለ የሰዉ ልጅ ዘር ላይ የደረሰዉን መከራ ማንም ኢትዮጵያዊ አይዘነጋዉም። በወቅቱ ‪#‎VOA‬ ‪#‎ESAT‬ ‪#‎ጀርመንራድዮ‬ ‪#‎ሕብር‬ ‪#‎ምኒልክ‬ሳልሳዊ ማህበራዊ ድረ ገፅ መረጃዉን ለህዝብ አዳርሰዋል። ዳሩ ግን የሚፈሰዉ ደም ዛሬም በተስፋዋ ምድር ኢትዮጵያ አልቆመም። ግፍ ሲበዛ ተስፋ ሲታጣ አማራጭ ሲዘጋ የጭቆና ቀንበር ሲጠብቅ የተዘጋዉን ለማስከፈት ቀንበሩን ለመስበር የሰዉ ልጅ ይነሳል።


በለጠ ጌታቸዉ ጋምቤላ ላይ በህወሃት ጥይት ወደቀ። ያች ቀን ለበለጠ እና ለወንድሞቹ ደግ ቀን አልነበረችም። ወንድሞቹ ወድቀዉ መነሳት አልቻሉም።በአንፃሩ ግን ለእሱ የተሻለች ነበረች። በደም ተነክሮም ቢሆን መነሳት ቻለ:: ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጭንቅ ታከመ
በህይዎት ቆየ። ለመታገልም ቆርጦ ተነሳ። ኤርትራ በረሃ ወረደ።


ጡረታ የወጡ የህወሃት የጦር መኮነኖች የመሬት ቅርምታቸዉን ለማስፈፀም በቀሰቀሱት ግጭት የብዙዎችን ህይዎት ቀጠፈ።የብዙዎችን ኑሮ አመሰቃቀለ:: ሀገራቸዉ ሁነዉ ሀገር አሳጣቸዉ:: ያ ግፍ እንደነ በለጠ ጌታቸዉ ያሉ ብርቱ ሰዎችን ወለደ:: በለጠ ስለፓለቲካ ስልጣን የሚያዉቀዉ ነገር አልነበረም::አንዱ ጨንቋኝ ሌላዉ ለምን ተጨቋኝ እንደሆነ ብዙም ግንዛቤ አልነበረዉም ::የሚያዉቀዉ ኢትዮጵያን ብቻ ነበር:: ዛሬ ላይ አንዱ ዘር አጥፊ ሌላዉ ጠፊ የሆነበት ምክንያት በመረዳቱ ቁስሉ ሳይደርቅ ለመፋለም ተቀለቀለን::ግፍ ሲበዛ…..ቁስለኛዉ አንበሳዉ በለጠ ..ለእኔ በኢትዮጵያ full of problem በሆነዉ የአማራ ትግል ..ገስግሶ መቀላቀሉ አስደስቶኛል.