የዘፋኙ ስብእና
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ዲሲ በሚገኝ አንድ የምሽት መዝናኛ ለጉድ ይጨለጣል፣ ጭፈራው ቀልጧል። ከመድረኩ በአንድ ታዋቂ ዘፋኝ በሚንቆረቆረው ዘፈን እስክስታውን ያስነኩት ከነበረው መካከል ሼኹ ይገኙበታል። ሼኹን አጅበው ከሚደንሱ አሽቃባጮች በመሽሎክሎክ አንድ በስፋት የሚታወቅ ዘፋኝ አብሯቸው ለመደነስ ሲሞክር በአሽቃባጮቹ ይገፈተራል። ደጋግሞ ሲሞክር ተመሳሳይ ግፍትሪያ ይፈፀምበታል። እንደምንም አልፎ አጠገባቸው ይደርስና አቅፎ ለመደነስ ሲሞክር ቱጃሩ ሼኽ አክክክ ብለው ፊቱ ላይ ይለጉዱበታል። ዘፋኙ ምን ቢያደርግ ጥሩ ነው? ከፊቱ ላይ በእጁ ጠርጎ ለሼኹ እያሳየ በምላሱ ጥርግ። ይህ ቀፋፊ ድርጊት በስፍራው የነበሩትን ቢያሳዝንም ሼኹ ግን በኩራት በሳቅ መንከትከታቸው አልቀረም። ይህን ምን ይሉታል!? የስብእና መዝቀጥ!?