ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል – በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በተለያዩ አንገብጋቢና ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቀት ያላቸውን ጦማሮችን ለንባብ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። አሁንም ወያኔ በጣም ሰፊ የአገራችንን መሬት እንደ ጣቃ ጨርቅ ቀዶ ለሱዳን ለመሸጥ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን መሠረት አድርገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአገር ሉዓላዊነትነና አንድነት ላይ ያደረገችንውን አስተዋጽዖዎችና የከፈለቻቸውን መስዋዕትነቶች አስመልክተው እጅግ ጠቃሚ ጦማር አቅርበዋል። ቀሲስ አስተርአየ በጽሁፋቸው አጽንኦት በመስጠት እንዲህ ብለዋል
“……ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገር የሚያዋስኗት ድንበሮችና፤ በውስጥም ዜጎቿ ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩባቸው ወሰኖች የፈረሱበት፤ ረዥም ዘመን የኖሩ ዛፎች የተጨፈጨቡት፤ መልሰው እንዳያቆጠቁጡ፤ (እንዳያንሰራሩ) ግንዶች ከነስራቸው የተነቀሉበት ዘመን ነው። ለ 25 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛው የወያኔ መንግሥት፤ አገሪቱን ከተቆጣጠረበት ቅጽበት ጀምሮ በቅርብ የሚታየው ከሩቅ የሚሰማው መፍረስና መገሰስ ቢሆንም፤ በየዘመኑ ድንበር እየጣሱ ከመጡ ወራሪዎች ጋራ ለዳር ድንበር ስትፋለም የኖረች ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውህዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ወቅት ምን ትላለች?የሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያውያን መካከል ብቻ ሳይወሰን፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚያውቁ በውጭ አገር ሊቃውንት መካከልም መነጋገሪያ ሆኗል። …..” ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል