በያዝነው 2016 በኢትዮጵያ ምግብ ማገኘት አስቸጋሪ እንደሚሆን በኢትዮጵያ የFAO ተጠሪ አማዱ አላሁሪ ገልፀዋል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት በእንግሊዘኛ ምህፃር «FAO» ፣ኢትዮጵያ የገጠማትን አስከፊ ድርቅ መቋቋም የሚያስችላት የ50 ሚሊዮን ዶላር አስቸኳይ የምግብ እርዳታ መጠየቁን ሮይተርስ ዘገበ።
በሀገሪቱ በዝናብ እጥረትና ከመጠን በላይ በጣለ ዝናብ ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 90 በመቶ ያህል ሰብል አልያዘም ።
ተቀማጭነቱን ሮም ያደረገዉ «FAO» እንዳስታወቀዉ በኢትዮጵያ የተከሰተዉ ድርቅ ብዙ የቀንድ ከብቶችን ገድሏል፤ ለ10.2 ሚሊዮን ሕዝብ ደግሞ የምግብ እጥረት ስጋትን ደቅኗል። ዝናብ ይጀምራል ተብሎ እስከ ሚጠበቅበት መጋቢት ድረስ የግጦሽ ሣርና ዉኃ አቅርቦት አሳሳቢነት ተባብሶ እንደሚቀጥል FAO ገልጿል። አሁን የሚታየው የምግብ ዋጋ መጨመር ፣የምግብ ክምችት እንዲሁም የምርታማነት መቀነስ የቀንድ ከብቶችም መዳከም ከቀጠለ በያዝነው 2016 በኢትዮጵያ ምግብ ማገኘት አስቸጋሪ እንደሚሆን በኢትዮጵያ የFAO ተጠሪ አማዱ አላሁሪ ገልፀዋል።
(ዶይቸ ቬለ)