አንድ የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ዛሬ ሞተ። በመሰላ አባድር ከተማ ደግሞ የአንድ ሌላ ተማሪ አስክሬን ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ተገኘ – VOA
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ንድፍ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ፣ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በሕዳር ወር አጋማሽ እንደገና ያገረሸው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን፣ በመሰላ ከተማ አባድር በተባለ ቦታ የአንድ ተማሪ አስክሬን ጉድጓድ ወድቆ መገኘቱን እንዲሁም አንድ የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ከፎቅ ላይ ወድቆ ሕይወቱ ማለፉን የኦሮምኛ ዝግጅት ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡ በምን ምክንያት ከፎቁ ላይ እንደወደቀ አለማወቃቸውን የገለጹ የዐይን እማኞች ከወደቀበት አንስተው ሆስፒታል እንደወሰዱት እዚያም እጃቸው ላይ ሕይወቱ እንዳለፈ ተናግረዋል፡፡ ዝርዝሩን ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች። ያድምጡ → listen