ዛሬም በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው እንደቀጠለ ውሏል።የኦሮሚያ ትምሕርት ቤቶች ከተወሰኑት ውጪ የመማር ማስተማር ሂደቶች ቆመዋል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
#Ethiopia #Oromoprotests : ዛሬም በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው እንደቀጠለ ውሏል።የኦሮሚያ ትምሕርት ቤቶች ከተወሰኑት ውጪ የመማር ማስተማር ሂደቶች ቆመዋል።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በትላንትናው እለት በተቃውሞ እና በቶክስ ስትናጥ የዋለቸው ኣምቦ ኣራት ነዋሪዎቿን በሞት ያጣች ሲሆን በኣምቦ ዩንቨርስቱ ኣውሮ ካምፓስ አንዲሁም በመናኻሪያ እና በቴሌኮምኒኬሽን ግቢ የሌንጮ ዲነቅሳ ሬሳዎች ሲገኙ ኣንድ ኣዛውንት ሴትም መገደላቸው ሲታወቅ በርካቶች ከባድ አና ቀላል የመቁሰል ኣደጋ ደርሶባቸዋል፥ በዛሬው አለት ኣምቦ ውጥረት ደምኖባት ውሏል።የወያኔ ወታደሮች የሌንጮ ዲነቅሳ ቀብር ኣምቦ በተወለደበት ኣከባቢ አንዳይሆን በመከልከል ከኣምቦ ውጪ በዋደሳ አንዲቀበር በሃይል ኣስገድደዋል።የኦሮሞ ልጆች በትውልድ ስፍራቸው አንዳይቀበሩ አየተደረገ ይገኛል።
ተቃውሞው በባኮ ባሌ ኣጋርፋ ተማሪዎች ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን የሕወሓት ወታደሮች ወደ ሕዝቡ በመተኮስ ጉዳት ሲያደርሱ በርካታ ተማሪዎችን እና ነዋሪዎችን ኣፍሰው ኣስረዋል።በሻሸመኔ ሉሲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተቃውሞ ተደርጓል።በጭሮ ጨርጨር ፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት ተቃውሞ የተሰማ ሲሆን ከተማውን ዘልቀው አንዳይገቡ ሲከለከሉ ተስተውሏል።በተለያዩ የኦሮሚያ ትምሕርት ቤቶች ከተወሰኑት ውጪ የመማር ማስተማር ሂደቶች ቆመዋል።#ምንሊክሳልሳዊ
