የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ በኦሮሚያ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው ። RDH
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ በኦሮሚያ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው ።
#RDH ጥር 4/2008
በምዕራብ ሃረርጌ መሰላ ወረዳ አባድር ከተማ ከሳምንት በፊት በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ከተሳተፈ በኃላ በመንግስት ሃይሎች ተይዞ ከተወሰደ በኃላ የት እንደወሰዱት ያልታወቀ የነበረው በሪ ሰኢድ አሊ የተባለ በዛሬው እለት ተገሎ ጫካ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱ ታወቀ


የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት የወሰደውንና እየወሰደ ያለውን ህገወጥ ተግባር በመቃወም እየተደረገ ያለው ተቃውሞ በተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሏል።

በምዕራብ ሃረርጌ ሃረማያ ዩኒቨርሲቲ እየተደረ ያለው ተቃውሞ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን የመንግስት ሃይሎችም በተማሪዎች ላይ የተለመደውን ህገ ወጥ እርምጃ በመውሰዳቸው ተማሪዎች ወደ አካባቢው ገበሬ ማህበረሰብ ሸሽተው በመሄድ መከለላቸው ታውቋል።
ይህ የመንግስት ሃይሎች ህገ ወጥ እርምጃ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የተካሄደ መሆኑም ተዘግቧል ።
በምእራብ ሀረርጌ እስኳሁን 263 ተማሪዎች የታሰሩ ሲሆን ብዛት ያላቸውም ቆስለው : በሃረማያ ሆስፒታልና በሃረማያ ህይወት ፋና ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ ታውቋል ።
በትላንትናው እለትም በሃረማያ አካባቢ የሚገኙ ሙዴ እና ቱጄ ገቢሳ የሚባሉ ገበሬ ማህበር ገበሬዎችም ከመንግስት ሃይሎች ጋር የተጋጩ ሲሆን የመንግስት ሃይሎች በወሰዱት እርምጃም አንድ ጫላ ሙሀመድ የሚባል ገበሬ መገደለሉንና በዛሬው እለትም የቀብር ስነስርአቱ መፈፀሙ ታውቋል ።
በአምቦ ከተማም አብደታ ኦላና የሚባል በመንግስት ሃይሎች የተገደለ ሰው : የቀብር ስነስርአቱ ሲፈፀም ረብሻ መፈጠሩ የታወቀ ሲሆን ህዝቡ የቀብር ስነስርአቱን በአግባቡ እንዳይፈፅም አስለቃሽ ጭስ የመንግስት ኀይሎች መተኮሳቸውንና በሰው ላይ ጉዳት ማድረሳቸው የታወቀ ሲሆን የተጎዱ ብዛት ያላቸው ሰዎችም አምቦ ሆስፒታል እየታከሙ መሆናቸውንና ከተጎዱት መካከልም አንዲት ህፃን ልጅ ከነ እናቷ እንደሚገኙበት ታውቋል ።
የአምቦ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ዶርሙ ተዘግቶባቸው መደብደባቸው ተሰምቷል ። በትላንትናው እለትም በሻሻመኔ የፕሪፓራቶሪ ተማሪዎች ተቃውሞ አካሄደዋል በዛሬው እለትም ግቢው ውስጥ ተሰባስበው ተቃውሟቸውን እያሳዩ መሆኑ ተዘግቧል ።
ባለፈው ሳምንት አዳባ ላይ ተጎድቶ ሻሸመኔ ሆስፒታል ተኝቶ የነበረው አወል በዛሬው እለት ህይወቱ ማለፋ ታውቋል ።
በትላንተ እለት ምስራቅ ወለጋ ሪሞ ወረዳ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ የፕሪፖራቶሪ ተማሪዎች : የታሰሩ ተማሪዎችና ሌሎችም ይፈቱ በሚል ድምፃቸውን ማሰማታቸው ታውቋል ።
በዛሬው እለትም በሀረር ተቃሞው የቀጠለ ሲሆን በሆሮ ጉድሩ ዞን አባዪ ጮማን ወረዳ ፊንጫ ከተማ ተማሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውሟቸውን አካሄደዋል
በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተቃውሞው ተፋፍሞ የቀጠለ ሲሆን ሶስት መቶ የሚደርሱተማሪዎች ታስረው እንደሚገኙና አንድ ተማሪም ቱዊንስ ሲ የሚባል ህንፃ ውስጥ መገደሉን የፀጥተ ሃይሎች ቦታውን ከበውት ሰለሚገኙ የሟቹን ማንነት ለመለየት አለመቻሉ ታውቋል ።
የአምቦ አዋሮ ካምፓስ ተማሪዎችም ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውንና ምግብም ሆነ መጠጥ እንዳይገባላቸው መከልከሉን ተዘግቧል ።
በተያያዘ ዜናም በትላንትናው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባደረገው ስብስባ የአዲስ አበባ ማሰተር ፕላን እንዲቆም ወስነናል ማለታቸውን ኢቢሲ የተባለው የመንግስት የቴሌቪዥን ጣቢያ የዘገበ ሲሆን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የትኛውን ማስተር ፕላን ነው ኦህዴዶች እንዲቆም የወሰኑት? አቶ አባዱላ በኢቢሲ ቀርበው ከ2006 ጀምሮ ቆሟል ያሉትን ነው ወይንስ ሌላም ህዝብ ያላወቀው ማስተር ፕላን አለ ሲሉ በመገረም ጠይቀዋል ። #RDH