Qabsoon itti fufa!! ‪በመላው ኦሮሚያ የትምህርት ማቆም ኣድማ ተደርጓል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን ኣምቦ ተቃውሞው ሲፈነዳ በመላው ኦሮሚያ የትምህርት ማቆም ኣድማ ተደርጓል።Qabsoon itti fufa!! ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ ‪#‎EPRDF‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ኣከባቢዎች ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በኣምቦ በማእከላዊ ሲሰቃይ ለሞት የተዳረገውን የኣብደታ ኦላንሳን ኣስከሬን ለመቅበር በተሰባሰቡ የኣምቦ ነዋሪዎች አና በወያኔ ወታደሮች መካከል ግጭት መፈጠሩ ታውቋል፤ አንዲሁም በ አምቦ ያለው ሁኔታ እጅግ ኣስጊ መሆኑን በመግልጽ ዝዐጎቻቸው ይሁኑ ሰራተኞቻቸው ወደ ኣምቦ አና ኣምቦ መስመር አንዳይሄዱ የኖርዋይ ኤምባሲ እና የተባበሩት መንግስታት-UNDSS ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።

በመላው ኦሮሚያ የትምህርት ማቆም ኣድማ ተደርጓል።ኣስተማሪዎች Qabsoon itti fufa!! መጻፋቸውን ተከትሎ በከፍተኛ ደርጃ በተስፋፋው ተቃውሞ ተማሪው ትምህርቱን ብማቆም ለነጻነቱ አና ለመብቱ ተቃውሞውን ቀጥሏል። በኣምቦ ዩንቨርስቲ ትላንትና ማምሻውን የሶስተኛ ኣመት የፋርማሲ ተማሪ ጋዳ ሳሙኤል በደህንነት ሃይሎች ታፍኖ ተወስዷል።የዩንቨርስቲው ኣዋሬ ካምፓስ ተማሪዎች ታግተው ያሉ ሲሆን ምግብ አንዳያገኙ ካፌው የተዘጋ መሆኑ ሲጠቆም ባለፈው ሁለት ቀን በሃሮማያ ዩንቨርስቲ የተደረገው ተማሪዎችን ኣግቶ በረሃብ የመቅጣት ድራማ አምቦ ላይ ተደግሟል።

በኣብደታ ኦላንሳ የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመገኘት የተሰባሰቡ ወጣቶች አና ሕጻናት ሳይቀሩ በሕወሓት ወታደሮች ጥይት ቆስለዋል። በቀብር ስነስርኣቱ ላይ ኣስለቃሽ ፖሊሶች ጭስ በመወርወር ሕዝቡን ሲበጠብጡት ተስተውላል። እዚያው ኣምቦ በመብራት ሃይል ግቢ ውስጥ የገባ ግለሰብን የወያኔ ወታደሮች ተከታትለው ገብተው በመታጠቢያ ቤት ውስጥ አንደገደሉት የኣይን ምስክሮች ተናግረዋል። በተጨማሪም በኀው ለሚ ውስጥ ወታደሮች ለተቃውሞ የወጡ ነዋሪዎች ላይ ሲተኩሱ አንደነበር ሲገለጽ የሻሸመኔ ፕሪፓራቶሪ ት\ቤት ተማሪዎች ወደ ከተማው ወጥተው ድምሽጻቸውን ያሰሙ ሲሆን የከተማው ፖሊስ ምንም ኣይነት አርምጃ ሳይወስድ ሰልፉን በጀርባ በመሆን አንዳጀበ ታውቋል፥ምናልባት የሰልፉን ኣስተባባሪዎች ለይቶ በጨለማ ለማፈን የተወጠነ ሴራ አንዳይሆን ስጋት የገባቸው ይናገራሉ። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.