ሕወሓትን ማመን ቀብሮ ነው። ….. የገበሬው የመኖር ሕልውና ሊረጋገጥ ይገባል። ‪(ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሕወሓትን ማመን ቀብሮ ነው። ….. የገበሬው የመኖር ሕልውና ሊረጋገጥ ይገባል። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterPlan‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎OPDO‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – እኛ ነገር የሚገባን መች ነው? የኦሮሞ ሕዝብ በፈጠረው ጫና ኣጣብቂኝ ውስጥ የገባው የሕወሓት ኣገዛዝ የማስተር ፕላኑን አቅድ ሰረዝኩት ኣለ። መሰረዙን ተከትሎ ተሰረዘ የሚሉ የቃላት ቅብብሎሽ ኣያየን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው።የኦሮሞ ሕዝብ ኣደባባይ ወጥቶ ተቃውሞን ማሰማቱ ያለው ኣገዛዝ ምን ያህል አንደተሽመደመድ በግልጽ ታይቷል።ሕዝቡ ማስተር ፕላኑ ብቻ ሳይሆን አየደረሰበት ያለው የፖለቲክ ጫና የኢኮኖሚ መድልዖ አንዲሁም የመልካም ኣስተዳደር ችግሮች አና የተለያዩ የሕልውና ጥያቄዎች አንዳልተመለሱለት ልናውቅ ይገባናል፥በልማት ስም ጥቂት የሕወሓት ሰዎች ሲዘርፉ ሕዝቡ የበይ ተመልካች መሆኑ ቁጣውን ኣገንፍሎታል።ማስተር ፕላኑ በሚዲያ ደረጃ ኣሊያም በኣገዛዙ ስብሰባዎች ተሰረዘ ተብሎ መደስኮሩ የገበሬው የመኖር ሕልውና ተረጋገጠ ብሎ የሚያስብ ካለ ተሳስቷል። ማስተር ፕላኑ በሕወሓት ልብ ውስጥ ኣልተሰረዘም።ይህንን ነቅተን ልናስብበት ይገባል።

Minilik Salsawi's photo.

ሕወሓት በተለይ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ በተለያዩ ክፍለጦሮች በሬጅመንት ደረጃ ስብሰባ በቡድን ቢሰበስብም ተቃውሞ ገጥሞታል አንዲሁም በደህንነት በኩልም የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የደህንነት ኣባላትን አና ጭፍረኛ ቅጥረኞቻቸው ላይ በኦሮሚያ ክልል በደረሰባቸው መገለል ያሰበውን ያህል ከመጠን ኣልፎ ሃይል ቢጠቀምም በፍጹም የሕዝቡን ተቃውሞ ሊያስቆመው ኣለመቻሉ አንዲሁም የዲያስፖራ ሕዝብ አና ሃገር ቤት ያለው ሕዝብ ዘር አና ጎሳ ሳይለይ ድጋፉን ለኦሮሞ ሕዝብ በማሳየቱ አና ኣጋርነቱን ስላሳየ ከኣጣብቂኙ ለመውጣት የዘየዳት ዘዴ የማስተር ፕላኑን እቅድ በፌዴራሉ ፓርላማ የተወሰነውን በክልል ፓርላማ መሻር ነው።የስልጣን ተዋረድ ይሁን ሃገራዊ መዋቅሩን ለወያኔ ኣገዛዝ እንተውለትና ዋናው ጉዳይ ግን ሰረዝኩት የሚለው ወያኔ ከኣጣብቂኙ ለመውጣት መሆኑን ማወቅ ኣለብን።

መሰረዙ አንደተጠበቀ ሆኖ ሕወሓት መሰሪ እና ቂመኛ አንደሆነ ማድረግ የሚፈልገው ኣዘናግቶ አንደሚያደርግ ማወቅ ኣለብን።ካለፉ ታሪኮችም መማር ኣለብን።ዛሬ የኣዲስ ኣበባን ማስተር ፕላን ሰረዝኩ ሲል እንደ ድል ቆጥረን በስሜት መናወዝ የለብንም።ዛሬ ኦሮሚያ በኣዲስ ኣበባ ላይ ያላትን ጥቅም እናስከብራለን ሲል ምን ኣስቦ ነው ብለን ልንመዝን ይገባናል፥ከኣዲስ ኣበባ ዙሪያ ያሉ ገበሬዎች ኣለመፈናቀላቸው የሚደገፍ ቢሆንም ወያነ በስልጣን ላይ አስካለ ድረስ ግን የመኖር ሕልውናቸው ስጋት ውስጥ አንደሆነ ልናውቅ ይገባል፤ከኣንድ ብሄር የተፈበረኩ የሪል ስቴት ባለሃብቶች በባለስልጣን ዘመዶቻቸው አየታገዙ በኦሮሞ ገበርዔዎች መሬቶች ላይ ሊዘምቱ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።የመሰረዙን ዜና ሰምተን አንደ ድል ኣድራጊ ከማጨብጨብ የኦሮሞ ወጣቶች የተሰዉት ለዘላቂ የኦሮሞ ገበሬዎች ሕልውና አስከሆነ ድረስ የመሰሪዎቹን አና ቂመኞቹን የሕወሓት ሰዎች ኣደገንነት ልናስብበት ይገባል፥ሕወሓትን ማመን ቀብሮ ነው። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬