ድሬዳዋ ዩንቨርስቲ በሕወሓት ወታደሮች ሲወረር ኣምቦ ሕዝቡና የሕወሓት ወታደሮች ተፋጠዋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ድሬዳዋ ዩንቨርስቲ በሕወሓት ወታደሮች ሲወረር ኣምቦ ሕዝቡና የሕወሓት ወታደሮች ተፋጠዋል።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎DireDawa‬ ‪#‎Ambo‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከባድ መሳሪያዎች የታጠቁ የሕወሓት ወታደሮች አና የፌዴራል ፖሊስ ኣባላት የድሬዳዋን ዩንቨርስቲ ወረውታል፤በቡድን ሆነው የሚሄዱ ተማሪዎችን አየደበደቡ ሲገኙ አስካሁን ከባድ ድብደባ የደረሰባቸው ሁለት ተማሪዎች ሆስፒታል ተወስደዋል። (ፎቶ ፋይል)

እንዲሁም በኣምቦ ከፍተኛ ውጥረት ያየለ ሲሆን በማዕከላዊ ድብደባ አና ግርፋት ደርሶበት ለሞት የተዳረገውን የኣምቦ ወጣት ኣብደታን ኣስከሬን ለመቀበል ሕዝቡ ግልብጥ ብሎ መውጣቱን ተከትሎ ቁጥራቸው አጅግ ለግምት የሚያስቸግር የሕወሓት ወታደሮች ከሕዝቡ ጋር ተፋጠው ይገኛሉ ። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ዘግይቶ የመጣ መረጃ አንደሚጠቁመው በአሁን ሰአት በአምቦ ከተማ የአብደታ ኦላንሳን አስክሬን ለመቀበል በወጣው ህዝብ ላይ ፌደራል ፓሊስ መተኮስ የጀመረ ሲሆን መብራት ሙሉ ለሙሉ በከተማይቱ ጠፍቷል።

Minilik Salsawi's photo.