ታላቅ የአጋርነት ጥሪ … ‹‹ዲያስፓራው የትግሉ የጀርባ አጥነት ሆኖ ይቀጥላል!››ድምፃችን ይሰማ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
‹‹ዲያስፓራው የትግሉ የጀርባ አጥነት ሆኖ ይቀጥላል!››ድምፃችን ይሰማ #Ethiopia
#1460DaysOfPeacefulStruggle #EthioMuslimDiaspora #EthioMuslims #EthioMuslimPeacefulStruggle
==== ታላቅ የአጋርነት ጥሪ ለዲያስፖራ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን!!!ማክሰኞ ጥር 3/2008 ====

የወሩን ሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር በትናንናው እለት ይፋ አድርገናል። መርሃ ግብሩ በቀጣይ ትግላችን አቅጣጫ ዙሪያ የሚደረግ ዘመቻ ሆኖ ‹‹የትግላችን ዓላማ ብሆራዊ ጭቆናን ማስወገድ ነው›› በሚል መሪ ቃል የሚተገበር ይሆናል። ብሄራዊ ጭቆናን እና የወደፊት ትግላችንን ስናስብ ዲያስፓራው ለትግላችን ያደረገውን አስተዋጽኦ እና ለትግሉም የጀርባ አጥንት መሆኑን አንዘነጋውም። በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደተገለጸው ዲያስፓራው የሙስሊሙ ህብረተሰብ የሚያደርገው ትግል ሂደት አጋር ብቻ ሳይሆን ባለድርሻም ነው። በመሆኑም ከዚሁ ሳምንት ጀምሮ የአራተኛው ዓመት መርሃ ግብሮች በዲያስፓራው ዘንድም በሰፊው እንዲተገብሩ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
እስከዛሬ በነበረው የትግል ሂደት ዲያስፖራው ልዩ ግብዓት ሆኖ እንደመቆየቱ መጠን አሁንም ይህን ሚናውን ‹‹ዲያስፓራው የትግሉ የጀርባ አጥነት ሆኖ ይቀጥላል!›› በሚል አጠቃላይ መሪ ቃል ስር የአራተኛውን ዓመት መርሃ ግብር እንዲተገብር አደራ እንላለን፡፡ ዲያስፖራው እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ የአጋርነት፣ የአንድነት እና የሰደቃ ዝግጅቶችን፣ በሙስሊሙ ጉዳይ የሚያወያዩ ጉባኤዎችን፣ ሰልፎችን፣ ለትግሉ እገዛ እና በመንግስት አረመኔያዊ እርምጃ ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን መደጎሚያ የሚሆን ገንዝብ ማሰባሰቢያ እና የመሳሠሉ ዝግጅቶችን በማካሄድ ለመሳተፍ የሚችል ሲሆን የትግላችን መሰረት አንድነታችን እና መተባበራችን መሆኑን ከግምት በማስገባት የሚያዘጋጃቸውን የውይይት መድረኮች በአገር፣ በአህጉር እና ብሎም በዓለም አቀፋዊ ደረጃ ከፍ በማድረግ አንድነቱን እና እርስ በርስ ተባባሪነቱን መግለጽ ይጠበቅበታል።
ትግላችን በአገራችን ደረጃ ለየት ላለ ሰላማዊ ትግል ፈር ቀዳጅ ከመሆኑ አንጻር አሁንም አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እና ለፍትህ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ዲያስፓራው ሙስሊም ህብረተሰብ ቀዳሚ ተሳታፊ በመሆን ለአገሩ አና ህዝቦቿ ያለውን አጋርነት ሊገልጽም ይችላል። ከላይ የተዘረዘሩት ተግባራት ለአብነት ያክል ያነሳናቸው ሲሆኑ የአገሩ ሁኔታ እና የማህበራት ግላዊ አቅም እና ሁኔታ በሚፈቅደው መጠን እና መልክ መርሃ ግብሮች ተፈጻሚ እንዲሆኑ በአላህ ስም እንጠይቃለን! በተጨማሪም በተለያዩ ማህበራት በሚተገበሩ መርሃ ግብሮች ዙሪያ የሚኖረውን የመረጃ ልውውጥ ያቀላጥፍ እና ለውይይትም ያግዝ ዘንድ የዋትስ አፕ ግሩፖች ይከፈታሉ። አንድ ግሩፕ ስራ የጀመረ እና ቁጥሩም ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ በሂደት ሌሎች ግሩፖችም የሚኖሩን ይሆናል።
‹‹ዲያስፓራው የትግሉ የጀርባ አጥነት ሆኖ ይቀጥላል!››
ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!