አንድነት በሙሉ የመተማመን እና የቅን ልቦና ላይ መመስረት ይገባል። ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አንድነት በሙሉ የመተማመን እና የቅን ልቦና ላይ መመስረት ይገባል። ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
#Ethiopia #Ethiopianoppositionparties #MinilikSalsawi #Unity
ሁላችንም ስለ አንድነት ብዙ ብለናል ጽፈናል ሰምተናል ኣንብበናል።ይሀ ውነት ግን በተግባር ከመተርጎም ይልቅ የኣንድ ሰሞን ጎዶሎ ሆይ ሆይታ ብቻ አንደሆነ ኣልፏል።ፖለቲከኞች የሕዝብን ስሜት ሳይሆን ተራሳቸውን ስሜት ባገናዘበ መልኩ የበላይነት ለመያዝ ሲባል ብቻ ስለ ኣንድነት ይሰብካሉ። ሊታረሙ የሚገቡ አና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሚያስገኙ ኣንድነቶችን ማጣጣም ኣለመቻሉ በጥቂቶች የበላይነት በብዙሃን የበታችነት የሚውተረተር የኣንድነት ሰበካ በመካሄዱም በላይ ጥቂቶች ራሳቸውን የኣንድነት ባላባት ኣድርገው ስለሚኮፍሱ ብቻ ሌሎች አጃቸው ሲሰበስቡ ከጋራ ኣብሮነት ይልቅ መዘበራረቅ አየቀደመ ችግር ፈጥሯል።
ዝም ተብሎ በባዶ ሜዳ ስለ ኣንድነት ግንዛቤ ኣልባ ሰበካ ቢካሄድ ኣሊያም ኣንድ ተቃውሞ በተነሳ ሰኣት አስከሚቀዘቅዝ ድረስ ስለ ኣንድነት አና ኣብሮ መስራት ቢሰበክ ምንም ፋይዳ የለውም፤ኣንድነት በመተማመን መንፈስ ለሕዝብ ባሰበ መንፈስ በቅን ልቦና መመስረት ከተቻለ ከፖለቲካ ኳኳታ እና የሆያ ሆዬ ፕሮፓጋንዳ ወጥቶ ሕዝብን በጋራ ማስተማር ማስተባበር ማደራጀት ማዋቀር ከተቻለ የኣንድነት ስኬቶች አንዲሁም ሕዝብ ስለመብቱ አና ነጻነቱ ኣውቆ ኣምባገነኖችን አንዲዋጋ ኣስታውጾ ያደርጋል።ኣንድ ኣላማ ኣለን የጋራ ጠላታችን ኣንድ ነው እስከተባለ ድረስ ኣንድነት ሳይኖረን ስለ ኣንድነት ኣንደበታችንን መክፈት እርግማን ነው ፤የሕወሓት ኣገዛዝ ይ፫ሕዝብ ብሶት ሲገነፍል ኣጀንዳው ስለመልካም ኣስተዳደር ሲሆን የለውጥ ሃይሉ ደሞ ስለ ኣንድነት ነው፤የሕዝብ ብሶት ሲቀዘቅዝ ኣብሮ ኣጀንዳውም ይቀዘቅዛል ይህ የሚያሳየው ስለ ኣንድነት ያለው መተማመን አና ቅን ልቦና ባዶ እና ለፕሮፓጋንዳ የተደገሰ መሆኑን ነው።
አስከዛሬ የተወሩ የተደሰኮሩ የተደረጉ ስምምነቶች ትብብሮች የጋራ የስራ ውሎች ሁሉ ግንዛቤ ኣልባ አና ተግባር ኣልባ ስለሆኑ የራስን የበላይነት ከመመኘት ብቻ የመነጩ የሕዝብን የጋራ ትግል ከውል ያላስገቡ ስለሁ ኣልተሳኩም።በዚህ ላይ ስለ ኣንድነት የሚሰብኩ ድርጅቶች ኣባሎቻቸው በድርጅታዊ ዲሲፒሊን ያልታነጹ እና በስድብ ፖለቲካ የተጀቦኑ መሆናቸው የጋራ መተማመኖችን እና ቅንነትን ስለሚያጠፉ ተዓማኒነትን ስለሚበርዙ ብዙሃኑን ለሽሽት ይዳርጉታል፥በመከባበር በመተሳሰብ እና በጋራ ፍቅር በኢትዮጵያዊነት ላይ ሲመረኮዙ የኣንድ ሰሞን ሆይሆይታን እና የፖለቲካ ፍጆታን ሳይሆን የሕዝብን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ለውጦች ለስኬት ይበቃሉ። #ምንሊሳልሳዊ