ሰላማዊ ትግሉ “አሁንም ተስፋ አስቆራጭ አይደለም” – የመድረክ ም/ል ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻው (VOA)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ



ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ሰሞኑን ኦሮሚያ ውስጥ በተፈጠረው ተቃውሞና አለመረጋጋት ምክንያት “ተገደለ” ያሉት ሰው ቁጥር ሰማንያ ዘጠኝ መድረሱን የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊው አቶ ጥላሁን እንደሻው ገልፀዋል።

አቶ ጥላሁን ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ ሰማንያ ዘጠኝ ሰው ስለመገደሉ ተጨባጭ ማስረጃ፣ ስምና አድራሻው የደረሣቸውና በተጨባጭ እናውቃለን ያሉትን እንጂ የሚያምኑት ከመቶ ሰው በላይ መገደሉን እንደሆነ አመልክተዋል።

“ኢሕአዴግ አሁን ስለ አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ከመናገር ይልቅ ማድረግ ያለበት ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር ተቀምጦ በሕገመንግሥቱ አንቀፅ 49 የተደነገገው ‘የኦሮምያ ክልል፣ የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀምንና የመሣሰሉትን ጉዳዮች…’ መነጋገር ነው” ብለዋል።

ኢሕአዴግ የፓርላማውን መቀመጫ ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠረበት ባለፈው ግንቦት በተካሄደው ምርጫ ማግስት ተቃዋሚዎችን እንደሚያሣትፍ የተናገረውን ለመተግበር ምን ያህል እየተንቀሣቀሰ እንደሆነ ተጠይቀው “ይህ አባባል ቀደም ሲልም የነበረ፤ በቃላት ብቻ የሚነገር ነው” ብለዋል።

የሰላማዊ ትግሉ ተስፋ አሁንም ተስፋ አስቆራጭ አይደለም ያሉት የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር እና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንደሻው ሌሎችም የኅብረተሰቡ ክፍሎች ከጎናቸው እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል። ዘገባውን ያዳምጡ → Listen