የሙስሊሙ ህብረተሰብ ትግል ብሄራዊ ጭቆናን ማስወገድን ዓላማው ያደረገ ነው!!! ድምፃችን ይሰማ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የሙስሊሙ ህብረተሰብ ትግል ብሄራዊ ጭቆናን ማስወገድን ዓላማው ያደረገ ነው!!!
#Ethiopia #1460DaysOfPeacefulStruggle #EthioMuslims #EthioMuslimPeacefulStruggle
በደልን የምንሸከምከምበት ትከሻ አይኖረንም! ድምፃችን ይሰማ እሁድ ጥር 1/2008
ለአራት አመታት የዘለቀውን እና ፍትህን እና የእምነት ነጻነታችንን አንግቦ የቀጠለውን ትግላችንን በማሰብ የሚካሄደው መርሃ ግብር እንደቀጠለ ይገኛል። የመጀመሪያው ሳምንት ላይ ይፋ የሆኑት መርሃ ግብሮች አመርቂ በሆነ መልኩ ተጠናቀዋል። የሁለተኛው ሳምንት መርሃ ግብራችን ይበልጥ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል፤ ኢንሻአላህ!
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መጠነ ሰፊ በሆነ እና በረቀቀ ስልታዊ ብሄራዊ ጭቆና ስር እንገኛለን። የሙስሊሙ ህብረተሰብ በአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ያለው ተሳትፎ እንዲመነምን እና በሂደት በድንቁርና እንዲኖር የሚያደርገው ፓሊሲ የሙስሊሙን ልጆች ከእምነታቸው እና ከትምህርታቸው አንዱን እንድመርጡ በሚያስገድዱ መመሪያዎች አማካኝነት ተፈጻሚ እንዲሆን እየተደረገ ይገኛል። ሙስሊም ሰራተኞች በእምነታቸው ግደታ የተደረገባቸውን ተግባራት በመፈጸማቸው ብቻ ከስራ ገበታቸው እንዲፈናቀሉ ይደረጋሉ። ግልጽ እና ግልጽ ባልሆኑ ዘዴዎች አማካኝነት ሙስሊሙ በአገሪቱ የንግድ እና የልማት ተሳትፎ እንዳይኖረው ተደርጓል። በአጭሩ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በእምነቱ አንገቱን እንዲደፋ እና እንዲያፍር የሚያደርጉ ሂደቶች ብዙ ናቸው፡፡ አምባገነኑ የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ ያወጀው ጭቆና አገሪቱ በውጥረት ላይ ባለችበት በአሁኑ ወቅትም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሙስሊሙን በአህባሽ አስተምህሮት የማጥመቅ ዘመቻው ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሙስሊሙ ህብረተሰብ ገንዘቡን፣ ላቡን እና በአብዛኛው ደሙን እያፈሰሰ ያቋቋማቸውን የእምነት ማእከላት ከሙስሊሙ ህብረተሰብ በመቀማት ጠፍጥፎ ለሰራው እና በሙስሊሙ ላይ ያወጀውን ብሄራዊ ጭቆና አስፈጻሚ አድርጎ ለሚጠቀመው አካል በመስጠቱ ላይም ገፍቶበታል።
ኢትዮዮጵያውያን ሙስሊሞች ከመጠን ያለፈውን ግፍ መሸከም የምንችልበት ትከሻ የለንም። በመሆኑም የዛሬ አራት አመት እምነታችን እና ማንነታችን ላይ ያነጣጠረውን የመንግስት እርምጃ በመቃወም የጀመርነው ትግል የተጫነብንን ብሄራዊ ጭቆና ሙሉ ለሙሉ ማስወገድን ዓላማው አድርጎ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የሁለተኛው ሳምንት መርሃ ግብራችንም ‹‹ትግላችን ብሄራዊ ጭቆናን ማስወገድ ነው!›› በሚል መርህ ስር የዚህን ብሄራዊ ጭቆና ዓይነቱን እና ይዘቱን መገምገም በሚያስችለን መልኩ መርሃ ግብሮችን እናካሂዳለን፡፡ እኩዩ ዘመቻ በህልውናችን ላይ እያደረሰ ባለው ተጽእኖ ዙሪያ ውይይቶችን እናደርጋለን፡፡ ይህን የመንግስት ሴራ በትክክል ላልተረዱ የህብረተስባችን ክፍሎች ገለጻ የምናደርግባቸውም የተለያዩ ዝግጅቶች ይኖሩናል፤ ኢንሻአላህ! ይኸው የሁለተኛ ሳምንት ዘመቻችን እስከፊታችን ጁሙዓ ጥር 6/2008 የሚዘልቅ ይሆናል።

በደልን የምንሸከምበት ትከሻ አይኖረንም!!!
ትግላችን ብሄራዊ ጭቆናን ማስወገድ ዓላማው ያደረገ ነው!!!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!