ሕዝብን ጥቂት ነውጠኛ ብሎ መፈረጅ የአገዛዙን ድንቁርና ይመሰክራል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi የወያኔው ስርኣት ተናግቶ በመላው አገሪቱ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱ እያየን እንገኛለን::ላለፉት ስምንት ሳምንታት በመላው የኦሮሚያ ክልል የተነሳው የሕዝብ ተቃውሞ የሕዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ሕዝብ ከዳር እስከዳር በሕብረት ሆ ብሎ መውጣቱ በቂ ማስረጃ እያለ ጥቂት ነውጠኞች በማለት ማጣጣል የወያኔ አገዛዝ ምን ያህል ለሕዝብ ንቀት እንዳለው ከማረጋገጡም በላይ የሕዝቡን አደባባይ ወጥቶ በገዛ ፍቃዱ ብሶቱ ገንፍሎ ተቃውሞ ማሰማቱ የጸረ ሰላም ሃይሎች ግፊት እና ቅስቀሳ ነው ብሎ መደስኮር አገዛዙ የፈጠረበትን ድንጋጤ ያሳያል::ጸረ ሰላም ብሎ አገዛዙ ከሚፈርጃቸው ከሚወነጅላቸው ድርጅቶች የበለጠ በፕሮፓጋንዳ ላይ ተሰማርቶ ሃሰት ሲነዛ የሚውለው የወያኔ አገዛዝ ራሱ መሆኑ መዘንጋቱ የሚገርም ጉዳያ ነው::ሕዝብን ጥቂት ነውጠኛ ብሎ መፈረጅ የአገዛዙን ድንቁርና ይመሰክራል::
በፖለቲካ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ መስክ እየተደበደበ እየተረገጠ በግፍ የሚገዛው ሕዝብ ብሶቱ ገንፍሎ አደባባይ ቢወጣ መሳሪያ ቢያነሳ ለመብቱ እና ለነጻነቱ እስከሆነ ድረስ ሊደገፍ ይገባዋል::የስርዓቱ የአንድ ለአምስት አደረጃጀት እና የጥቃቅን አነስተኛ የጆሮ ጠቢነት ፖሊሲን ጥሶ መብቱን ለማስከበር እና ወያኔ በቃኝ በማለት ተቃውሞ ያሰማው ሕዝብ ብዙሃኑ መሆኑን ከተገደሉት ከታሰሩና ከተደበደቡት ቁጥሮች መገመት ቀላል ነው::ከሕጻን እስከ አዋቂ ከተማሪ እስከ ገበሬ የተሳተፈበት ይህ ተቃውሞ ማንም አልፈጠረውም:: የአገዛዙ ፖሊሲዎች እና አስፈጻሚ ካድሬዎች እንዲሁም የስርዓቱ ውሸትን የሚረጩ ባለስልጣናት እና ሚዲያዎች የፈጠሩት ችግር ነው::ያልተሰራ ያልተፈጠረ ያልተደረገ ተደረገ በማለት እንዲሁም ተማሪውን ገበሬውን ሰራተኛው በማፈናቀል በማሰር በማሳደድ በመግደል በእዳ በመያዝ በተለያየ መንገድ ጥቃት እያደረሱ ጥቂቶች ተጠቃሚ የሆኑበት ይህ እኩይ/ክፉ ስርዓት ሕዝቡ ብሶቱን አገንፍሎታል::
መፍትሄው ደሞ አንድ ነው ስርነቀል ለውጥ:: በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ የፖለቲካ ጉዳዮች ሁሉም እኩል ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል::ማንም ከማንም አያንስም::ወታደራዊ እና ደህንነቱ ክፍል ከአንድ ብሄር የበላይነት መላቀቅ አለበት::ነገ የሚመጣው አደጋ የስርዓቱ ጀሌዎች አይሸከሙትም:: የሕዝብ ብሶት እየገነፈለ ስለሆነ ሕዝባዊ መንግስት ማቋቋም መፍትሄው ነው::ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሕግ ፊት እኩሉ ሆኖ የሕግ የበላይነት ሊረጋገጥ ይገባል::ሕዝብ በየትኛውን የኢትዮጵያ ክልሎች ተዘዋውሮ የመስራት የመኖር መብት ሊኖርው ይገባል::ለዜጎች ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል::ልማት የሚጠላ እድገትን የሚቃወም ማም ኢትዮጵያዊ የለምሖንም ግን ምስኪን ገበሬዎች እየተፈናቀሉ ለጎዳና እየተዳረጉ ለረሃብ እየተጋለጡ የሚያፈናቅላቸው ልማት ማንም አይደግፈውም::ሁሉም ሕዝብ ለዚህ ነው የወያኔ ልማት በአፍንጫዬ ይውጣ የሚለው::የወያኔ ልማት ብዙሃኑን ገድሎ ጥቂቱን የሚያሳድግ ስለሆነ ማንም አይደግፈውም:: ሕዝብን ጥቂት ነውጠኛ ብሎ መፈረጅ የአገዛዙን ድንቁርና ይመሰክራል:: ይህንን የተንገዳገደ የተነቃነቀ ስርዓት በአፋጣኝ በጋራ ሆነን ተረባርበን ልናስወግደው ይገባል::#ምንሊክሳልሳዊ