አዲስ አበባን ዝጋ ዘመቻ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


 Millions of voices for freedom - UDJ's photo.

 

ገዚው ፓርቲ የሕዝብ ጥያቄ ከማክበር ይልቅ ፣ ብሄራዊ መግባባት እንዲፈጠር ከመስራት ይልቅ ፣ የሃይል እርምጃ በመዉሰድ የተነሱ ተቃዉሞዎችን ለመጨፍለቅ ወስኑዋል። በዚህም ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ፡ኢትዮጵያዉያን በኦሮሚያ በግፍና በጭካኔ ተገድለዋል። ከሺሆች የሚቆጠሩ ታስረዋል።

ይህ ትግል ዉጭ አገር ያሉ ትግል አይደለም። ዉጭ አገር ያሉ ድጋፍ ያደርጋሉ እንጂ ትግሉ በዋናነት የሕዝቡ ትግል ነው። ይህ ትግል ለመብት፣ ለነጻነት፣ ለፍትህ የሚደረግ ትግል ነው። ይህ ትግል የአንድ ብሄረሰብ ወይም የአንድ አካባቢ ሳይሆን የኢትዮጵያዉይን ሁሉ ትግል ነው።

በትእቢት ያበጡ ገዢዎች ለሆዳቸው ባደሩ ወታደሮቻቸውና በያዙት ጠመንጃ ይመካሉ። ነገር ግን አንርሳ፣ እነርሱ ጥቂቶች ናቸው። እኛ ሚሊዮኖች ነን። እኛ በሁሉም ቦታዎች ከተንቀሳቀሰን፣ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ለሕዝብ ጥያቄ ይንበረከካሉ።

ወያኔዎ ለመግደል ሲመጡ ላለመገደል ራስን መከላከል ጠቢብነት ነው። ከወያኔ አጋዚ ጭፍጨፋ ለመከላከል፣ ዉጤት የሚያመጣ ሰላማዊ የሆነ ስትራቲጂ መንገድ የመዝጋት እንቅስቃሴ ነው። ደግመን እንናገራለን ፣ ይሄ ሰላማዊ የሆነ እንቅስቃሴ ነው። በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አይደርስም። ገዳዮች ግፍ እንዳይፈጽሙ የማከላከል እንቅስቃሴ ነው።

በዚህም ምክንያት አዲስ አበባን ከሌሎች ከተሞች የሚያገናኙትን መንገዶች በድንጋይ፣ በዛፍ፣ በጎማ በመሳሰሉት በመዝጋት ገዳዮችን የማዳከም እንቅስቃሴ ተጀምሩዋል። በአዲስ አበባ ዙሪያ የተጀመረዉም በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ይቀጥላል

(እባክዎ ይህ መልዕክት በስፋት እንዲሰራጭ ያግዙ)