አርሰናል ፈራሚውን ይፋ ሊያደርግ ስለመዘጋጀቱ እንዲሁም ሌሎች የተጠናቀቁ እና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ የዝውውር ዜናዎች


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


imageየማለዳ ትኩስ የዝውውር ዜናዎች – ታህሳስ 29፣ 2008 ዓ.ም – Ethio Addis Sport. #Ethihopia #Miniliksalsawi

አርሰናል የጥር ወር የመጀመሪያ ፈራሚውን ይፋ ሊያደርግ ስለመዘጋጀቱ እንዲሁም ሌሎች የተጠናቀቁ እና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ የዝውውር ዜናዎችን ይዘናል

ግብፃዊ አማካኝ መሐመድ አልኒኒይ ከባስል ክለብ ወደኤመራትስ ለማምራት ጫፍ ላይ ይገኛል። ዝውውሩም እርግጥ ለመሆን በእጅጉ ተቃርቧል።

የአርሰን ቬንገር ተጫዋቾች ከ12 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያቸው የሚሆነውን ዋንጫ ለማንሳት በመልካም ሁኔታ ወደፊት እየገፉ የሚገኝ ሲሆን፣ የመድፈኞቹ አለቃም የመሃል ክፍላቸው ተጨማሪ ተጫዋች እንደሚይስፈልገውም ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ሊቨርፑል ባለበት የተከላካይ ተጫዋቾች ጉዳት የተነሳ በጥር ወር ዝውውር መስኮቱ ወቅት ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዳለበት ገልፀዋል።

የቀዮቹ አሰልጣኝ ኮሎ ቱሬና ደያን ሎቭረንም የተለመደው ጉዳት የነካቸው በመሆኑ በቡድናቸው ውስጥ ምንም ዓይነት በጥሩ አቋም ላይ የሚገኝ የመሃል ተከላካይ የላቸውም። ነገር ግን ረቡዕ ዕለት የሰርቢያዊውን ወጣት ማርኮ ግሩጂችን ዝውውር አጠናቀዋል።

ወደሌሎች ዜናዎች ስናመራ…

ሳም አላርዳይስ በሰንደርላንድ አሰልጣኝነት ዘመናቸው የመጀመሪያው የሆነ ተጫዋች አስፈርመዋል። ተጫዋቹም የባየር ሙኒክ ተከላካዩ ጃን ኪርቾፍ ነው።

የሳውዛምፕተኑ አሰልጣኝ ሮናልድ ኪዩመን ማኔ የማይሸጥ ተጫዋች መሆኑን ለፈላጊዎቹ አስረግጠው ተናግረዋል።

ጆ ኮል ለኮንቨንትሪ ሲቲ ክለብ በቋሚነት ፈርሟል።

የሊቨርፑሉ ተከላካይ ቲያጎ ኢሎሪ በአስቶንቪላ የነበረው የውሰት ቆይታ እንዲቋረጥ ተደርጎ ወደሊቨርፑል እንዲመለስ ተደርጓል።

ኤቨርተኖች በ3 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ስምምነት የወደፊቱ ጆርዳን ሻኪሪ የተባለውን ወጣት ተጫዋች፣ ሻኒ ታርሻጅን ዝውውር አጠናቋል።

ማንችስተር ዩናይትድ 40 ሚ.ፓ ዋጋ ያለውን የኤቨርተኑን አጥቂ ራሞሉ ሉካኩን ለማስፈረም እየተከታተሉ ይገኛሉ።

በመጨረሻም ቀያይ ሰይጣኖቹ በዶርትሙንድ በውሰት ላይ የሚገኘውን አድናንን ዣኑዛይ የውሰት ቆይታ ከወዲሁ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል።

የዕለቱ የማለዳ የዝውውር ዜናዎቹ እነዚህ ነበሩ አበቃና ቀኑንን ሌላሎች ትኩስ የዝውውር ዜናዎች ካሉ ይዘን እንመጣለን መልካም ቀን ይሁንላችሁ።

http://ethioaddissport.com/2016/01/08/%E1%8B%A8%E1%88%9B%E1%88%88%E1%8B%B3-%E1%89%B5%E1%8A%A9%E1%88%B5-%E1%8B%A8%E1%8B%9D%E1%8B%8D%E1%8B%8D%E1%88%AD-%E1%8B%9C%E1%8A%93%E1%8B%8E%E1%89%BD/