ኢራን የሚደርስባት የዲፕሎማሲ ኪሳራ እየጨመረ መሆኑ ታወቀ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


 

 

አብደላህ ኢብን አብደላህ's photo.የተለያዩ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ድጋፋቸዉን ለሳዑዲ አረቢያ እየሰጡ ነዉ። ሱዳን፣ጅቡቲ፣ ኳታር፣ባህሬን፣የተባበሩት አረብ ኢምሬትስና፣ቱርክ በይፋ ከሳዑዲ አረቢያ ጎን ቆመናል እያሉ ነዉ። ዮርዳኖስ ሳዑዲን በመደገፍና ኢራንን በመቃወም ካሉት አገራት ተርታ እራሷን አሰልፋለች።

የኢራንን ፍላጎት በሟሟላት የሚታወቁት ቻይናዎች አብዛኛዉ የነዳጅ ዘይት ፍጆታቸዉ የሚሞላዉ በሳዑዲ አረቢያ በመሆኑ ኢራንን የመደገፍ አዝማሚያ አላሳዩም። ሌላዋ የኢራን አጋር የሆነችዋ ራሽያ አገራቱን ለማሸማገል ኢንጂ ከአንዱ ጎን የመቆም ፍላጎቷን አላሳየችም።

ሳዑዲ አረቢያ ከሙስሊም አገራት የምታገኘዉ ድጋፍ እየጨመረ ባለበት ወቅት የኔቶ አባል የሆነችዋ ብቸኛ ሙስሊም አገር ቱርክ ፕሬዝዳንት በሳዑዲ ላይ የሚቀርበዉ ወቀሳ የተጋነነ መሆኑን ይገልጻሉ።የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኢድሮጋንን ኢራንን የሚደግፉ እና ሳዑዲን የሚተቹ ቡድኖችን ማስጠንቀቃቸዉ ታዉቋል።

“በሶሪያ ዉስጥ ለሚደረገዉ ግድያ ዝም ያሉ ሁላ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ አንድ ሰዉ በመገደሉ እየተንጫጩ ነዉ።በሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የተደረገዉ የሞት ቅጣትን ተቀበላቹትም አልተቀበላቹትም የሳዑዲ የዉስጥ ጉዳይ ነዉ” ሲሉ የቱርክ ፕሬዝዳንት አቋማቸዉን ይፋ ማድረጋቸዉ ታዉቋል።ኢድሮጋን አክለዉም ሳዑዲ የሞት ፍርድ ከፈረደችባቸዉ 47ሰዎች መካከል 46 ሱኒ መሆናቸዉን፤ አንዱ ብቻ ሺዓ መሆኑን በመግለጽ ዉሳኔዉየሳዑዲ አረቢያ የዉስጥ ጉዳይ መሆኑን በድጋሚ አጽን ኦት ሰጥተዋል።

ዮርዳኖስ ንጉስ አብደላህ አቻቸዉን የሳዑዲዉን ንጉስ ሰልማን በትላንትናዉ እለት ደዉለዉ ማናገራቸዉ የታወቀ ሲሆን፥ አማን ሙሉ ትብብሯን ከሪያድ ጋር እንደምታረግም መግለጻቸዉ ታዉቋል።ንጉስ አብደላህ በኢራን የሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ ላይ የተደረገዉን ጥቃት በመቃወም ድርጊቱን ለማዉገዝ አማን የኢራንን አምባሳደር ጠርታ ማናገሯን ለንጉስ ሰልማን ገልጸዋል።

የመካከለኛዉ ምስራቅ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ፣ የሰላምና መረጋጋትን ሁናቴ የሚተነትኑ ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት የሺዓ አገራትና የሺዓ መሪዎች ለአካባቢዉ ሰላምና መረጋጋት መደፍረስ ተጠያቂ ናቸዉ ይላሉ። ኢራን መካከለኛ ምስራቅ እንዳይረጋጋ ችግር ትፈጥራለች በማለት ይገልጻሉ።

በኢራቅ የነበረዉ አናሳዉ የሱኒዉ የሳዳም ሁሴን መንግስት ከወደቀ ጀምሮ መንበረ ስልጣኑንን የያዙት ሺዓ ኢራቃዉያን ለከፍተኛ የርስ በርስ እልቂት ተጠያቂ ናቸዉ በማለትም ጨምረዉ ያስረዳሉ። በሶሪያ የ አባታቸዉን ስልጣን የተረከቡት “አለዋት” የሚባለዉ አናሳ የሺዓ እምነት ቅርንጫፈ ተከታይ የሆኑት በሻር አል-አሳድ አብላጫዉ ሱኒ በሆነበት አገር የዘር ማትፋጥፋትን እየፈጸሙ ነዉ ሲሉ ይከሳሉ። በሊባኖስ በሀሰን ነስረላህ የሚመራዉ የሺዓ የሒዝቡላህ ታጣቂ ሐይል የሰፈረበት ቦታ ከእስራኤል ቅርብ በመሆኑ ሒዝቡላህ በሚፈጥራቸዉ ችግሮች የሱኒዉን የሊባኖስ ማህበረሰብ በእስራ ኤል ያስጨፈጭፋል ብለዉ ከምክሰስም ባሻገር፤ ከእስራኤል ጋር በመመሳጠር የሱኒ ሊባኖሳዉያንን ድልድይ፣ግንባታ ያስፈርሳል፣ የቀድሞዉን የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስቴር ረፊቀል ሀሪሪን አስገድሏል ሲሉ የመካከለኛው ምስራቅ ግጭቶችን ያጠኑ ሱኒ ተንታኞች ይገልጻሉ።

ኢራን ዉስጥ ያሉ ሱኒዎች በኢራን መንግስት ከፍተኛ በደልና ጭቆና እንደሚደርስባቸዉ የሰባዊ መብት ድርጅቶች ያስረዳሉ። ባለፍዉ አመት ብቻ ኢራን እስከ 1000 የሚደርሱ ሰዎችን በሞት ፍርድ መቅጣቷን አምኒስቲ ኢንተርናሽናል አሳዉቋል። በኢራን ዉስጥ ያሉ 27ሱኒ የሐይማኖት አስተማሪዎችና አክቲቪስቶች ባለፈዉ የአዉሮፕያዉያኑ አመት መገባደጃ የሞት ፈርድ እንደተፈረደባቸዉ ታዉቋል። ባለፍዉ የአዉሮፕያዉያኑ አመት መገባደጃ ሸህራም አሃዲ የተባሉ ሱኒ የሐይማኖት አስተማሪ በሞት ሲቀጡ በሱኒ አገራት ዉስጥ ልክ ኢራናዉያንን በሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲና ቆንስላ ጽህፈት ቤት የፈጸሙትን ጥቃት አይነት አለመፈጸማቸዉ ይታወቃል።

የኢራን ዜጎች ተመሳሳይ የኤምባሲ ጥቃት ሲፈጽሙ ይህ የመጀመሪያዉ አይደለም። በጥቅምት 24/1972 በኢራን ተማሪዎች የሚመራ የታጣቂዎች ቡድን አሜሪካ ኤምባሲን ሰብሮ በመግባት በዉስጡ ያሉትን ዲፕሎማቶችና ጠባቂዎች ለ444 ቀናት ኤምባሲዉን ተቆጣጥሮ ማገቱ ይታወቃል።የኢራን ዜጎች ዳግም 36 አመታት በሗላ የሳዑዲ ኤምባሲ ላይ ጥቃት በማድረሳቸዉ ኢራን በመካከለኛዉ ምስራቅዉስጥ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ አጣብቂኝ ደርሶባታል። ሁለቱ አገራት ፍጥጫ ዉስጥ ናቸዉ። ፍጥጫቸዉ በመላዉ አለም ያሉትን ሱኒ እና ሺዓዎች በመስመር የሚከፋፍል እየሆነ ነዉ። ከዘጠና ከመቶ በላይ የሚሆኑት የአለማችን ሱኒ ሙስሊሞች “በቃ!” በማለት ማበርና መተባበር የጀመሩ ይመስላል።