በኣሰቦት አና ፈንታሌ መተሃራ ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የገና የምሳ ምግባቸውን ባይኮት ኣድርገው ጥለው ወጥተዋል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
#Ethiopia #Oromoprotests :ተቃውሞው ዛሬም ቀጥሎል፥በኣሰቦት አና ፈንታሌ መተሃራ ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የገና የምሳ ምግባቸውን ባይኮት ኣድርገው ጥለው ወጥተዋል።#MinilikSalsawi
በሸዋ ፈንታሌ መተሃራ ገበሬዎች እና ተማሪዎች አንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች በጋራ በመሆን ለተቃውሞ ኣደባባይ በመውጣት አንዲሁም በሃረርጌ ኣሰቦት የሚገኙ ገበሬዎች ተማሪዎች አና የከተማው ነዋሪ በሃሙስ ገበያ በመሰባሰብ ገበያቸውን ትተው በኣዲስ ኣበባ ማስተር ፕላን ላይ እና በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚደረገውን ግድያ በመቃወም ኣውግዘዋል።ይህ በእንዲህ አንዳለ የጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለገና በኣል የቀረበላቸውን ምሳ ባለመመገም ተቃውማቸውን ያሳዩ መሆኑ ታውቁል። Minilik Salsawi
